bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 24
Psalms 24
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
የዳዊት መዝሙር ። ምድርና ሞላዋ የጌታ ናቸው፥ ዓለምና በእርሷም የሚኖሩ ሁሉ።
2
እርሱ በባሕሮች ላይ መሥርቶአታልና፥ በፈሳሾችም ላይ አጽንቶአታልና።
3
ወደ ጌታ ተራራ ማን ይወጣል? በቅድስናውስ ስፍራ ማን ይቆማል?
4
እጆቹ የነጹ፥ ልቡም ንጹሕ የሆነ፥ ነፍሱን ለከንቱ ያላነሣ፥ በሽንገላ ያልማለ።
5
እርሱ ከጌታ ዘንድ በረከትን ከመድኃኒቱ አምላክም ጽድቅን ይቀበላል።
6
ይህች ትውልድ እርሱን የምትፈልግ ናት፥ የያዕቆብን አምላክ ፊት የምትፈልግ።
7
እናንት በሮች ራሳችሁን ከፍ አድርጉ፥ የዘለዓለም ደጆችም ተከፈቱ፥ የክብርም ንጉሥ ይግባ።
8
ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው? ጌታ ነው፥ ብርቱና ኃያል፥ ጌታ ነው፥ በሰልፍ ኃያል።
9
እናንተ በሮች ራሳችሁን ከፍ አድርጉ፥ የዘለዓለም ደጆችም ይከፈቱ፥ የክብርም ንጉሥ ይግባ።
10
ይህ የክብር ንጉሥ ማን ነው? የሠራዊት ጌታ እርሱ የክብር ንጉሥ ነው።
← Chapter 23
Chapter 25 →