bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 147
Psalms 147
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
ጌታን አመስግኑ፥ መዝሙር መልካም ነውና። ለአምላካችን ምስጋና ያማረ ነው።
2
ጌታ ኢየሩሳሌምን ይሠራል፥ ከእስራኤልም የተበተኑትን ይሰበስባል።
3
ልባቸው የተሰበረባቸውን ይፈውሳል፥ ሕማማቸውንም ይጠግናል።
4
የከዋክብትንም ብዛት ይቈጥራል፥ ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል።
5
ጌታችን ታላቅ ነው፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፥ ለጥበቡም ቍጥር ስፍር የለውም።
6
ጌታ የተዋረዱትን ያነሣል፥ ክፉዎችን ግን እስከ ምድር ድረስ ያዋርዳል።
7
ለጌታ በምስጋና ዘምሩ፥ ለአምላካችንም በመሰንቆ ዘምሩ፥
8
ሰማዩን በደመናት ይሸፍናል ለምድርም ዝናብን ያዘጋጃል፥ ሣርን በተራሮች ላይ ያበቅላል።
9
ለእንስሶችም ምግባቸውን ይሰጣል ለሚጠሩት ለቁራዎች ጫጩቶችም እንዲሁ።
10
በፈረስ ኃይል አይደሰትም፥ በሰውም ጡንቻ ሐሴት አያደርግም።
11
ጌታ በሚፈሩት፥ በጽኑ ፍቅሩ በሚታመኑት ይደሰታል።
12
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ጌታን አመስግኚ፥ ጽዮንም ሆይ፥ ለአምላክሽ እልል በዪ
13
የደጆችሽን መወርወሪያ አጽንቶአልና፥ ልጆችንም በውስጥሽ ባርኮአልና።
14
በወሰንሽም ሰላምን አደረገ፥ የስንዴንም ስብ አጠገበሽ።
15
መልእክቱን ወደ ምድር ይልካል፥ ቃሉም እጅግ ፈጥኖ ይሮጣል።
16
አመዳዩን እንደ ባዘቶ ይሰጣል፥ ጉሙን እንደ አመድ ይበትነዋል፥
17
በረዶውን እንደ ፍርፋሪ ያወርዳል፥ በቁሩ ፊት ማን ይቆማል?
18
ቃሉን ልኮ ያቀልጠዋል፥ ነፋሱን ያነፍሳል፥ ውኆችንም ያፈስሳል።
19
ቃሉን ለያዕቆብ፥ ሥርዓቱንና ፍርዱን ለእስራኤል ይናገራል።
20
ለሌሎች አሕዛብ ሁሉ እንዲህ አላደረገም፥ ፍርዱንም አልገለጠላቸውም። ሃሌ ሉያ።
← Chapter 146
Chapter 148 →