bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 14
Psalms 14
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር። አላዋቂ በልቡ፦ አምላክ የለም ይላል። በሥራቸው ረከሱ፥ ጐሰቈሉ፥ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም።
2
የሚያስተውል እግዚአብሔርንም? የሚፈልግ እንዳለ ያይ ዘንድ ጌታ ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመለከተ።
3
ሁሉም ዐመፁ በአንድነትም ረከሱ፥ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም፥ አንድም እንኳ የለም።
4
ክፉ አድራጊዎች አያስተውሉምን? እንጀራን እንደሚበሉ ሕዝቤን የሚያኝኩ፥ ጌታን አይጠሩምን፥
5
እዚያም ታላቅ ፍርሃት ይዞአቸዋል፥ አግዚአብሔር በጻድቃን ዘንድ ነውና፥
6
የምስኪኖችን ዕቅድ ታዛባላችሁ፥ ጌታ ግን መጠለያቸው ነው፥
7
ከጽዮን መድኃኒትን ለእስራኤል ማን ይሰጣል? ጌታ የሕዝቡን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥ ያዕቆብ ደስ ይለዋል፥ እስራኤልም ሐሤት ያደርጋል።
← Chapter 13
Chapter 15 →