bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 124
Psalms 124
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
የዳዊት የዕርገት መዝሙር። ጌታ ከእኛ ጋር ባይሆን እስራኤል እንዲህ ይበል፦
2
ጌታ ከእኛ ጋር ባይሆን ሰዎች በእኛ ላይ በተነሡ ጊዜ፥
3
ቁጣቸው በላያችን በነደደ ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ ሕያዋን ሳለን በዋጡን ነበር፥
4
በዚያን ጊዜ ውኃ ባሰጠመን ነበር፥ በነፍሳችንም ላይ ወራጅ ውኃ ባለፈ ነበር፥
5
በዚያን ጊዜ የጐርፍ ውኃ በነፍሳችን ላይ ባለፈ ነበር።
6
ለጥርሳቸው ንክሻ ያላደረገን ጌታ ይመስገን።
7
ነፍሳችን እንደ ወፍ ከአዳኞች ወጥመድ አመለጠች፥ ወጥመድ ተሰበረ እኛም አመለጥን።
8
ረድኤታችን ሰማይንና ምድርን በሠራ በጌታ ስም ነው።
← Chapter 123
Chapter 125 →