bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 114
Psalms 114
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
ሃሌ ሉያ! እስራኤል ከግብጽ፥ የያዕቆብም ቤት ከእንግዳ ሕዝብ በወጣ ጊዜ፥
2
ይሁዳ መቅደሱ፥ እስራኤልም ግዛቱ ሆነ።
3
ባሕር አየች፥ ሸሸችም፥ ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ።
4
ተራሮች እንደ አውራ በጎች፥ ኮረብቶችም እንደ ጠቦቶች ዘለሉ።
5
አንቺ ባሕር የሸሸሽው፥ አንቺስ ዮርዳኖስ ወደ ኋላሽ የተመለስሽው፥ ምን ሆናችሁ ነው?
6
እናንተም ተራሮች፥ እንደ አውራ በጎች፥ ኮረብቶችስ፥ እንደ ጠቦቶች ለምን ዘለላችሁ?
7
በያዕቆብ አምላክ ፊት፥ በጌታ ፊት ምድር ተናወጠች፥
8
ዐለቱን ወደ ውኃ መቆሚያ፥ ድንጋዩንም ወደ ውኃ ምንጭ ይለውጣል።
← Chapter 113
Chapter 115 →