bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Psalms 108
Psalms 108
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
የዳዊት የምስጋና መዝሙር።
2
አምላኬ ሆይ ልቤ ጽኑ ነው፥ እቀኛለሁ፥ በክብሬም እዘምራለሁ።
3
በገና ሆይ፥ ተነሥ፥ መሰንቆም እንዲሁ፥ እኔም ማለዳን ልቀስቅሰው።
4
አቤቱ፥ በአሕዛብ መካከል አመሰግንሃለሁ፥ በሕዝቦችም መካከል እዘምርልሃለሁ፥
5
ጽኑ ፍቅርህ በሰማይ ላይ ታላቅ ናትና፥ እውነትህም እስከ ደመናት ድረስ ነውና።
6
አቤቱ፥ በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ በል፥ ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ትሁን።
7
ወዳጆችህ ይድኑ ዘንድ፥ በቀኝህ አድን አድምጠኝም።
8
እግዚአብሔር በመቅደሱ ተናገረ፦ “ደስ እያለኝ ሴኬምንም እከፋፍላለሁ፥ የሱኮትንም ሸለቆ እሰፍራለሁ።
9
ገለዓድ የእኔ ነው ምናሴም የእኔ ነው፥ ኤፍሬም የራሴ መከላከያ ቁር ነው። ይሁዳ በትረ መንግሥቴ፥
10
ሞዓብ መታጠቢያዬ ነው፥ በኤዶምያስ ላይም ጫማዬን እዘረጋለሁ፥ በፍልስጥኤም ላይ ድሌን ዐውጃለሁ።
11
ወደ ጽኑ ከተማ ማን ይወስደኛል? እስከ ኤዶምያስ ድረስስ ማን ይመራኛል?
12
አቤቱ፥ የጣልኸን አንተ አይደለህምን? አምላክ ሆይ፥ ከሠራዊታችን ጋር መውጣት አቆምህ።
13
በጥቃታችን ድረስልን፥ የሰውም ማዳን ከንቱ ነው።
14
በእግዚአብሔር ኃይልን እናደርጋለን፥ እርሱም የሚያስጨንቁንን ይረጋግጣቸዋል።”
← Chapter 107
Chapter 109 →