bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Joshua 19
Joshua 19
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
ሁለተኛውም ዕጣ ለስምዖን ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ፤ ርስታቸውም በይሁዳ ልጆች ርስት መከከል ነበረ።
2
እነዚህም ርስታቸው ሆኑላቸው፤ ቤርሳቤህ፥ ሤባ፥ ሞላዳ፥
3
ሐጸርሹዓል፥ ባላ፥ ዔጼም፥
4
ኤልቶላድ፥ በቱል፥ ሔርማ፥
5
ጺቅላግ፥ ቤትማርካቦት፥ ሐጸርሱሳ፥
6
ቤተ-ለባኦት፥ ሻሩሔን፤ ዐሥራ ሦስት ከተሞችና መንደሮቻቸው፤
7
ዐይን፥ ሪሞን፥ ዔቴር፥ ዓሻን፤ አራት ከተሞችና መንደሮቻቸው፤
8
እስከ ባዕላት-ብኤርና እስከ ደቡቡ ራማት ድረስ በእነዚህ ከተሞች ዙሪያ ያሉ መንደሮች ሁሉ። የስምዖን ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።
9
የይሁዳ ልጆች ግዛት በሆነው ክፍል ውስጥ የስምዖን ልጆች ርስት ሆነ፥ የይሁዳም ልጆች ድርሻ ስለ በዛባቸው የስምዖን ልጆች በርስታቸው መካከል ወረሱ።
10
ሦስተኛውም ዕጣ ለዛብሎን ልጆች በየወገኖቻቸው ወጣ፤ የርስታቸውም ድንበር እስከ ሣሪድ ደረስ ይደርስ ነበር፤
11
ድንበራቸውም በምዕራብ በኩል ወደ መርዓላ ወጣ፥ እስከ ደባሼትም ደረሰ፤ በዮቅንዓም ፊት ለፊት ወዳለው ወንዝ ደረሰ፤
12
ከሣሪድም ወደ ፀሐይ መውጫ ወደ ምሥራቅ ወደ ኪስሎትታቦር ዳርቻ ዞረ፤ ወደ ዳብራትም ወጣ፥ ወደ ያፊዓም ደረሰ፤
13
ከዚያም በምሥራቅ በኩል ወደ ጋት-ሔፍርና ወደ ዒታ-ቃጺን አለፈ፤ ወደ ሪምን በመውጣት ወደ ኒዓ ታጠፈ፤
14
ድንበሩም በሰሜን በኩል ወደ ሐናቶን ዞረ፥ መጨረሻውም በይፍታሕ-ኤል ሸለቆ ነበረ።
15
ቀጣት፥ ነህላል፥ ሺምሮን፥ ይዳላ፥ ቤተልሔም፤ ዐሥራ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
16
የዛብሎን ልጆች ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
17
አራተኛውም ዕጣ ለይሳኮር ልጆች በየወገኖቻቸው ወጣ።
18
ድንበራቸውም የሚያጠቃልለው ኢይዝራኤልን፥ ከስሎትን፥ ሱነምን፥
19
ሐፍራይምን፥ ሺኦንን፥ አናሐራትን፥
20
ረቢትን፥ ቂሶንን፥ አቤጽን፥
21
ሬሜትን፥ ዐይን-ጋኒምን፥ ዐይን-ሐዳን፥ ቤት-ጳጼጽን ነበረ፤
22
ድንበሩም ወደ ታቦርና ወደ ሻሕጹማ፥ ወደ ቤት-ሳሚስ ደረሰ፥ የድንበራቸውም መጨረሻ ዮርዳኖስ ነበረ፤ ዐሥራ ስድስት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
23
የይሳኮር ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
24
አምስተኛውም ዕጣ ለአሴር ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ።
25
ድንበራቸውም ሔልቃት፥ ሐሊ፥ ቤጤን፥ አክሻፍ፥
26
አላሜሌክ፥ ዓምዓድ፥ ሚሽአል ነበረ፤ በምዕራብ በኩል ወደ ቀርሜሎስና ወደ ሺሖር-ሊብናት ደረሰ፤
27
ወደ ፀሐይም መውጫ ወደ ቤትዳጎን ዞረ፥ ወደ ዛብሎንም ወደ ይፍታሕኤል ሸለቆ፥ በሰሜን በኩል ወደ ቤት-ዔሜቅና ወደ ንዒኤልም ደረሰ፤ ከዚያም ወደ ሰሜን ወደ ካቡል ወጣ፤
28
ከዚያም ወደ ዔብሮን፥ ወደ ረዓብ፥ ወደ ሐሞን፥ ወደ ቃና እስከ ታላቁ ሲዶናም ደረሰ።
29
ድንበሩም ወደ ራማ፥ ወደ ተመሸገውም ከተማ ወደ ጢሮስ ዞረ፤ ድንበሩም ወደ ሖሳ ዞረ፤ መጨረሻውም በአክዚብ በኩል ወደ ባሕሩ ነበረ፤
30
ዑማ፥ አፌቅ፥ ረዓብ ደግሞ ነበሩ፤ ሀያ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው።
31
የአሴር ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
32
ስድስተኛውም ዕጣ ለንፍታሌም ልጆች በየወገኖቻቸው ወጣ።
33
ድንበራቸውም ከሔሌፍ፥ በጸዕነኒም ካለው ከባሉጥ ዛፍ፥ ከአዳሚ-ኔቄብ፥ ከየብኒኤል እስከ ለቁም ድረስ ነበረ፤ መጨረሻውም በዮርዳኖስ ነበረ።
34
ድንበሩም ወደ ምዕራብ ወደ አዝኖት-ታቦር ዞረ፥ ከዚያም ወደ ሑቆቅ ወጣ፤ ከዚያም በደቡብ በኩል ወደ ዛብሎን፥ በምዕራብ በኩል ወደ አሴር፥ በዮርዳኖስም በፀሐይ መውጫ ወደ ይሁዳ ደረሰ።
35
የተመሸጉትም ከተሞች እነዚህ ነበሩ፤ ጺዲም፥ ጼር፥ ሐማት፥ ረቃት፥ ኬኔሬት፥
36
አዳማ፥ ራማ፥ አሦር፥
37
ቃዴስ፥ ኤድራይ፥ ዐይን-ሐጾር፥
38
ይርኦን፥ ሚግዳል-ኤል፥ ሖሬም፥ ቤት-ዓናት፥ ቤት-ሳሚስ፤ ዐሥራ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው።
39
የንፍታሌም ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
40
ሰባተኛውም ዕጣ ለዳን ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ።
41
የርስታቸውም ግዛት የሚያጠቃልለው፤ ጾርዓን፥ ኤሽታኦልን፥ ዒር-ሼሜሽን፥
42
ሸዕለቢንን፥ ኤሎንን፥ ይትላን፥
43
ኤሎንን፥ ትምናን፥ አቃሮንን፥
44
ኢልተቄን፥ ገባቶንን፥ ባዕላትን፥
45
ይሁድን፥ ብኔ-ብረቅን፥ ጋት-ሪሞንን፥
46
ሜያ-ርቆንን፥ በኢዮጴ ፊት ለፊት ካለው ዳርቻ ጋር ራቆንን ነበር።
47
የዳንም ልጆች ግዛታቸውን መቆጣጠር ባለልቻሉ ጊዜ ከሌሼም ጋር ሊዋጉ ወጡ፥ ያዙአትም፥ በሰይፍም ስለት መቱአት፥ ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም፤ ሌሼም የነበረውን ስምዋንም በአባታቸው በዳን ስም ዳን ብለው ጠሩአት።
48
የዳን ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው።
49
ምድሩንም ሁሉ በየግዛቱ ርስት እንዲሆን አከፋፍለው ከጨረሱ በኋላ፥ የእስራኤል ልጆች ለነዌ ልጅ ለኢያሱ በመካከላቸው ርስት ሰጡት።
50
በኤፍሬም ተራራማ አገር ያለችውን እንዲሰጡት የጠየቃቸውን ተምናሴራ የምትባለውን ከተማ እንደ ጌታ ትእዛዝ ሰጡት፤ ከተማም ሠርቶ ተቀመጠባት።
51
ካህኑ አልዓዛር፥ የነዌም ልጅ ኢያሱ፥ የእስራኤልም ልጆች ነገዶች የአባቶች አለቆች በጌታ ፊት በሴሎ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በዕጣ ያከፋፈሉት ርስት ይህ ነው። ምድሪቱንም አከፋፍለው ጨረሱ።
← Chapter 18
Chapter 20 →