bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Joshua 16
Joshua 16
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
የዮሴፍም ልጆች ዕጣ በኢያሪኮ ወንዝ አጠገብ በምሥራቁ በኩል ካለው ከዮርዳኖስ አንሥቶ በምድረ በዳው አድርጎ ከኢያሪኮ በተራራማው አገር በኩል ወደ ቤቴል ወጣ፤
2
ከቤቴል ወደ ሎዛ ወጣ፥ በአርካውያንም ግዛት በኩል ወደ ዓጣሮት አለፈ፥
3
ወደ ምዕራብም እስከ የፍሌጣውያን ድንበር እስከ ታችኛው ቤትሖሮን ድንበር እስከ ጌዝር ድረስ ወረደ፥ መጨረሻውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ።
4
የዮሴፍም ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ርስታቸውን ወረሱ።
5
የኤፍሬምም ልጆች ድንበር በየወገኖቻቸው እንደዚህ ነበረ፤ በምሥራቅ በኩል የርስታቸው ድንበር አጣሮትአዳር እስከ ላይኛው ቤትሖሮን ድረስ ነበረ፤
6
ከዚያም ተነሥቶ ድንበሩ ወደ ባሕሩ በኩል ወጣ፤ በሰሜን በኩል ሚክምታት ይገኝ ነበር፤ ድንበሩም ወደ ምሥራቅ ወደ ተአናትሴሎ ዞረ፥ ወደ ኢያኖክ በምሥራቅ በኩል አለፈ፥
7
ከኢያኖክም ወደ አጣሮትና ወደ ነዓራት ወረደ፤ ወደ ኢያሪኮም ደረሰ፥ መጨረሻውም ዮርዳኖስ ነበር።
8
ድንበሩም ከታጱዋ ወደ ምዕራብ እስከ ቃና ወንዝ ድረስ አለፈ፥ መጨረሻውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ። የኤፍሬም ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።
9
ይኸውም በምናሴ ልጆች ርስት መካከል ለኤፍሬም ልጆች ከተለዩ ከተሞች ጋር፥ እነዚህም ከተሞች ሁሉ ከመንደሮቻቸው ጋር ርስታቸው ነበሩ።
10
በጌዝርም የተቀመጡትን ከነዓናውያንን አላሳደዱአቸውም፥ እስከ ዛሬም ድረስ ከነዓናውያን በኤፍሬም መካከል ተቀምጠዋል፤ እነርሱም የጉልበት ሥራ የሚሠሩ ባሮች ሆነዋል።
← Chapter 15
Chapter 17 →