bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Job 35
Job 35
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
ኤሊሁም ደግሞ ቀጠለ፤ እንዲህም አለ፦
2
“ይህ ትክክል ነው ብለህ ታስባለህን? ወይስ፦ በእግዚአብሔር ፊት እኔ ጻድቅ ነኝ ትላለህን?
3
አንተ፦ ምን ትጠቀማለህ? ኃጢአት ባልሠራስ ምን እጠቀማለሁ? ብለህ ጠይቀሃልና።
4
እኔ ለአንተና ከአንተ ጋር ላሉትም ባልንጀሮችህ እመልሳለሁ።
5
ዐይኖችህን ወደ ሰማይ አቅንተህ እይ፥ ከአንተም በላይ ከፍ ያሉትን ደመናት ተመልከት።
6
ኃጢአት ብትሠራ ምን ትጐዳዋለህ? መተላለፍህስ ቢበዛ ምን ታደርገዋለህ?
7
ጻድቅስ ብትሆን ምን ትሰጠዋለህ? ወይስ ከእጅህ ምንን ይቀበላል?
8
ክፋትህ እንደ አንተ ያለውን ሰው ይጐዳዋል፥ ለሰውም ልጅ ጽድቅህ ይጠቅመዋል።
9
ከግፍ ብዛት የተነሣ ሰዎች ይጮኻሉ፥ ከኃያላንም ክንድ የተነሣ ለእርዳታ ይጣራሉ።
10
ነገር ግን፦ በሌሊት የደስታ መዝሙሮችን የሚለግስ፥ ከምድርም እንስሶች ይልቅ የሚያስተምረን ከሰማይም ወፎች ይልቅ ጥበበኞች የሚያደርገን
11
ፈጣሪዬ እግዚአብሔር ወዴት ነው? የሚል የለም።
12
በዚያ ስለ ክፉ ሰዎች ትዕቢት ይጮኻሉ፥ እርሱ ግን አይመልስላቸውም።
13
በእውነት እግዚአብሔር ከንቱ ነገርን አይሰማም፥ ሁሉን የሚችል አምላክም አይመለከተውም፥
14
እንዲያውም፦ ‘አላየውም፥ ጉዳዩ በእርሱ ፊት ነው፥ እኔም አጠብቀዋለሁ’ ስትልማ የባሰ ነው።
15
አሁን ግን በቁጣው ስላልቀጣ፦ ትዕቢት ምን እንደሆነ የማያውቅ መሰለህ?
16
ስለዚህ ኢዮብ ከንቱ ንግግርን ከአፉ ያወጣል፥ ያለ እውቀትም ቃሉን ያበዛል።”
← Chapter 34
Chapter 36 →