bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Job 11
Job 11
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
ናዕማታዊውም ሶፋር መለሰ፤ እንዲህም አለ፦
2
“በውኑ ነገር ለሚያበዛ መልስ መስጠት አይገባምን? ወይስ ተናጋሪ ሰው እንደ ጻድቅ ይቈጠራልን?
3
ከንቱ ልፍለፋህ ሰዎችን ዝም ያሰኛቸዋልን? ብትሳለቅስ የሚያሳፍርህ የለምን?
4
አንተ፦ ትምህርቴ የተጣራ ነው፥ በዓይንህም ፊት ንጹሕ ነኝ ትላለህ።
5
ምነው እግዚአብሔር ቢናገርህ! በአንተም ላይ ከንፈሩን ቢከፍት!
6
የጥበቡን ምሥጢር ቢገልጥልህ! ማስተዋሉ እጥፍ ነውና። እግዚአብሔር ለበደልህ ከሚገባው አሳንሶ እንደሚያስከፍልህ እወቅ።”
7
“የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ልትመረምር ትችላለህን? ሁሉን የሚችል አምላክን ፍጻሜ ልትመረምር ትችላለህን?
8
ከሰማይ ይልቅ ከፍ ይላል፥ ምን ልታደርግ ትችላለህ? ከሲኦልም ይልቅ ይጠልቃል፥ ምን ልታውቅ ትችላለህ?
9
ርዝመቱ ከምድር ይልቅ ይረዝማል፥ ከባሕርም ይልቅ ይሰፋል።
10
እርሱ ቢያልፍ፥ ቢዘጋም፥ ጉባኤንም ቢሰበስብ፥ የሚከለክለው ማን ነው?
11
የማይረቡ ሰዎችን ያውቃልና፥ በደልንም ሲያይ ዝም ብሎ አይመለከትም።
12
የሜዳ አህያ ሰው ሆኖ ሲወለድ፥ ከንቱ ሰው ጥበብን ያገኛል።”
13
“አንተ ልብህን ቅን ብታደርግ፥ እጆችህን ወደ እርሱ ትዘረጋለህ፥
14
በእጅህ በደል ቢኖር አርቀው፥ በድንኳንህም ኃጢአት አይኑር፥
15
በዚያን ጊዜ በእውነት ፊትህን ያለ ነውር ታነሣለህ፥ ትበረታለህ፥ አትፈራምም።
16
መከራህንም ትረሳለህ፥ እንዳለፈ ውኃ ታስበዋለህ።
17
ሕይወትህ ከቀትር ይልቅ ያበራል፥ ጨለማም ቢሆን እንደ ጥዋት ይሆናል።
18
ተስፋም ስላለህ ተማምነህ ትቀመጣለህ፥ በዙሪያህ ትመለከታለህ ፥ በደኅንነትም ታርፋለህ።
19
ትተኛለህ፥ የሚያስፈራህም የለም፥ ብዙ ሰዎችም ልመና ያቀርቡልሃል።
20
የክፉዎች ዐይን ግን ትጨልማለች፥ የሚሸሹበትንም ያጣሉ፥ ተስፋቸውም ነፍስን አሳልፎ መስጠት ነው።”
← Chapter 10
Chapter 12 →