bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Hosea 12
Hosea 12
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
ኤፍሬም በሐሰት፥ የእስራኤልም ቤት በተንኰል ከበበኝ፤ ይሁዳ ግን እስካሁንም ከጌታ ጋር ይመላለሳል ለቅዱሱም ታማኝ ነው።
2
ኤፍሬም ነፋስን ያሰማራል፥ ቀኑን ሙሉ የምሥራቅን ነፋስ ይከተላል፤ ሐሰትንና ዓመጻን ያበዛል፤ ከአሦር ጋር ቃል ኪዳን ያደርጋሉ፥ ወደ ግብጽም ዘይት ይወስዳሉ።
3
ጌታም ደግሞ ከይሁዳ ጋር ሙግት አለው፥ ያዕቆብንም እንደ መንገዱ ይቀጣል፤ እንደ ሥራውም ይመልስለታል።
4
በማኅፀን ውስጥ ወንድሙን በተረከዙ ያዘው፥ በጉልማስነቱም ጊዜ ከአምላክ ጋር ታገለ፤
5
ከመልአኩም ጋር ታግሎ አሸነፈ፤ አልቅሶም ለመነው። በቤቴልም አገኘው፥ በዚያም ከእርሱ ጋር ተነጋገረ።
6
እርሱም የሠራዊት አምላክ ጌታ ነው፤ የመታሰቢያው ስም ጌታ ነው።
7
“ስለዚህ ወደ አምላክህ ተመለስ፤ ጽኑ ፍቅርንና ፍርድን ጠብቅ፥ ዘወትርም በአምላክህ ታመን።”
8
ከከነዓን ወገን ነው፤ በእጁ የተንኰል ሚዛን አለ፥ ሽንገላንም ይወድዳል።
9
ኤፍሬምም፦ “በእውነት ባለ ጠጋ ሆኜአለሁ፥ ሀብትንም አግኝቻለሁ፥ በድካሜም ሁሉ ኃጢአት የሚሆን በደል አያገኙብኝም” አለ።
10
እኔም ጌታ፥ ከግብጽ ጀምሬ አምላክህ ነኝ፤ እንደ ዓመት በዓል ቀን እንደገና በድንኳን እንድትኖር አደርግሃለሁ።
11
ለነቢያትም ተናግሬአለሁ፥ ራእይንም አብዝቻለሁ፤ በነቢያትም እጅ ምሳሌዎችን ሰጥቻለሁ።
12
ኃጢአት በገለዓድ አለ፤ ፈጽመው ከንቱ ናቸው፤ በሬዎችን በጌልገላ ይሠዋሉ፥ መሠዊያዎቻቸውም በእርሻ ትልሞች ላይ የድንጋይ ክምር ይሆናሉ።
13
ያዕቆብ ወደ አራም ምድር ሸሸ፥ እስራኤልም ስለ ሚስት አገለገለ፥ ስለ ሚስትም በጎችን ያሰማራ ነበረ።
14
ጌታም በነቢይ እጅ እስራኤልን ከግብጽ አወጣ፥ በነቢያትም እጅ ጠበቀው።
15
ኤፍሬም አስመርሮ አስቆጣው፤ ስለዚህ ደሙ በላዩ ላይ ነው፤ ጌታውም ስድቡን በራሱ ላይ ይመልሳል።
← Chapter 11
Chapter 13 →