bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Genesis 35
Genesis 35
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
እግዚአብሔርም ያዕቆብን አለው፦ “ተነሥተህ ወደ ቤቴል ውጣ፥ በዚያም ኑር፥ ከወንድምህ ከዔሳው ፊት በሸሸህ ጊዜ ለተገለጠልህ ለእግዚአብሔርም መሠውያውን ሥራ።”
2
ስለዚህ ያዕቆብ ለቤተሰቡና ከእርሱ ጋር ላሉት ሁሉ እንዲህ አለ፦ “እንግዶቹን አማልክት ከመካከላችሁ አስወግዱ ንጹሐንም ሁኑ፥ ልብሳችሁንም ለውጡ፥
3
ተነሥተንም ወደ ቤቴል እንውጣ፥ በዚያም በመከራዬ ጊዜ ለሰማኝ፥ በሄድሁበትም መንገድ ከእኔ ጋር ለነበረው ለእግዚአብሔር መሠውያን እሠራለሁ።”
4
እነርሱም በእጃቸው ያሉትን ባዕዳን አማልክት ሁሉ፥ እንዲሁም በጆሮአቸውም ያሉትን ጉትቾች ለያዕቆብ ሰጡት፥ ያዕቆብም በሴኬም አጠገብ ካለችው የባሉጥ ዛፍ በታች ቀበራቸው።
5
ተነሥተውም ሄዱ፥ የእግዚአብሔርም ፍርሃት በዙሪያቸው ባሉት ከተሞች ሁሉ ወደቀ፥ የያዕቆብንም ልጆች ለማሳደድ አልተከተሉአቸውም።
6
ያዕቆብም፥ እርሱ ከእርሱ ጋርም የነበሩት ሰዎች ሁሉ፥ በከነዓን ምድር ወዳለችው ወደ ሎዛ መጡ፥ እርሷም ቤቴል ናት።
7
በዚያም መሠዊያውን ሠራ፥ የዚያንም ቦታ ስም “ኤልቤቴል” ብሎ ጠራው፥ እርሱ ከወንድሙ ፊት በሸሸበት ጊዜ እግዚአብሔር በዚያ ተገልጦለት ነበርና።
8
የርብቃ ሞግዚት ዲቦራም ሞተች፥ በቤቴልም ከባሉጥ ዛፍ በታች ተቀበረች፥ ስሙም “አሎንባኩት” ተብሎ ተጠራ።
9
እግዚአብሔርም ለያዕቆብ ከፓዳን-ኣሪም ከተመለስ በኋላ እንደገና ተገለጠለት፥ ባረከውም።
10
እግዚአብሔርም፦ “ስምህ ያዕቆብ ነው፥ ከእንግዲህም ወዲህ፥ ስምህ እስራኤል ይባል እንጂ፥ ስምህ ያዕቆብ ተብሎ አይጠራ፥” አለው። ስሙንም እስራኤል ብሎ ጠራው።
11
እግዚአብሔርም አለው፦ “ሁሉን ቻይ አምላክ እኔ ነኝ፥ ብዛ፥ ተባዛም፥ ሕዝብና የአሕዛብ ማኅበር ከአንተ ይሆናል፥ ነገሥታትም ከጉልበትህ ይወጣሉ።
12
ለአብርሃምና ለይስሐቅም የሰጠኋትን ምድር ለአንተ እሰጣለሁ፥ ከአንተም በኋላ ለዘርህ ምድሪቱን እሰጠለሁ።”
13
እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ከተነጋገረበት ስፍራ ወደ ላይ ወጣ።
14
ያዕቆብም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር በተነጋገረበት ቦታ የድንጋይ ዐምድ አኖረ፤ የመጠጥ መሥዋዕትንም በእርሱ ላይ አፈሰሰ፥ ዘይትንም አፈሰሰበት።
15
ያዕቆብም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር የተነጋገረበትን ያን ቦታ ቤቴል ብሎ ጠራው።
16
ከቤቴልም ተነሡ፥ ወደ ኤፍራታም ሊደርሱ ጥቂት ሲቀራቸው ራሔልን ምጥ ያዛት፥ በምጡም ተጨነቀች።
17
ምጡም ባስጨነቃት ጊዜ አዋላጂቱ፦ “አትፍሪ፥ ይኸኛው ደግሞ ወንድ ልጅ ይሆንሻልና” አለቻት።
18
እርሷም ስትሞት ነፍስዋ በምትወጣበት ጊዜ ስሙን “ቤንኦኒ” ብላ ጠራችው፥ አባቱ ግን ብንያም አለው።
19
ራሔልም ሞተች፥ ወደ ኤፍራታ በምትወስድም መንገድ ተቀበረች፥ እርሷም ቤተልሔም ናት።
20
ያዕቆብም በመቃብርዋ ላይ ሐውልት አቆመ፥ እርሱም እስከ ዛሬ የራሔል የመቃብርዋ ሐውልት ነው።
21
እስራኤልም ከዚያ ተነሣ፥ ድንኳኑንም ከዔዴር ግንብ ባሻገር ተከለ።
22
እስራኤልም በዚያች አገር በተቀመጠ ጊዜ ሮቤል ሄደ የአባቱንም ቁባት ባላን ተገናኛት፥ እስራኤልም ሰማ። የያዕቆብም ልጆች ዐሥራ ሁለት ናቸው፥
23
የልያ ልጆች፥ የያዕቆብ በኩር ልጅ ሮቤል፥ ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዛብሎን፥
24
የራሔል ልጆች፥ ዮሴፍና ብንያም ናቸው።
25
የራሔል አገልጋይ የነበረችው የባላ ልጆች፥ ዳንና ንፍታሌም ናቸው።
26
የልያ ባርያ የዚልፋ ልጆችም፥ ጋድ፥ አሴር ናቸው። እነዚህ በፓዳን-ኣሪም በሶርያ የተወለዱለት የያዕቆብ ልጆች ናቸው።
27
ያዕቆብም ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ ወደ መምሬ፥ አብርሃምና ይስሐቅ እንግዶች ሆነው ወደ ተቀመጡባት፥ ወደ ቂርያት-አርባ፥ እርሷም ኬብሮን ወደምትባለው መጣ።
28
የይስሐቅም ዕድሜ መቶ ሰማንያ ዓመት ሆነ።
29
ይስሐቅም ነፍሱን ሰጠ፥ ሞተም፥ ሸምግሎ ዕድሜንም ጠግቦ ወደ ወገኖቹ ተከማቸ፥ ልጆቹም ዔሳውና ያዕቆብ ቀበሩት።
← Chapter 34
Chapter 36 →