bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Ezekiel 15
Ezekiel 15
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
የጌታ ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦
2
የሰው ልጅ ሆይ፥ በዱር ዛፎች መካከል ያለው የወይን ቅርንጫፍ፥ ከሁሉም ዛፎች ይልቅ የወይን ግንድ የሚበልጠው እንዴት ነው?
3
ማንኛውም ሥራ ለመስራት እንጨት ከእርሱ ይወስዳል? ወይስ ሰዎች ዕቃ የሚንጠለጠልበትን ኩላብ ከእርሱ ይወስዳሉን?
4
እነሆ ለመቃጠል ለእሳት ተስጥቷል፥ እሳቱም ሁለቱን ጫፎቹን በልቶታል፥ መካከሉም ተቃጥሏል፥ ለሥራ ይጠቅማልን?
5
እነሆ ደህና ሳለ ለሥራ ካልጠቀመ፥ ይልቁንስ እሳት ከበላውና ከተቃጠለ በኋላ ሥራ ይሠራበታልን?
6
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዱር ዛፎች መካከል ያለውን የወይን ግንድ እሳት እንዲበላው እንደ ሰጠሁት፥ እንዲሁ በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን አሳልፌ እሰጣለሁ።
7
ፊቴን በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ፥ ከእሳት ቢያመልጡም፥ እሳት ግን ይበላቸዋል፥ ፊቴን በእነርሱ ላይ ባደረግሁ ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።
8
እምነተ ቢስ ሆነዋልና ምድሪቱን ባድማ አደርጋታለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
← Chapter 14
Chapter 16 →