bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
Ecclesiastes 6
Ecclesiastes 6
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
ከፀሐይ በታች ያየሁት ክፉ ነገር አለ፥ እርሱም በሰው ላይ እጅግ የከበደ ነው።
2
እግዚአብሔር ለሰው ሀብትን፥ ንብረትንና ክብርን ሰጠው፥ ከወደደውም ነገር ሁሉ ለነፍሱ አልጐደለውም፤ ነገር ግን ሌላ ሰው ይበላዋል እንጂ ከእርሱ ይበላ ዘንድ እግዚአብሔር ሥልጣን አልሰጠውም፤ ይህም ከንቱና ክፉ ደዌ ነው።
3
ሰው መቶ ልጆች ቢወልድ፥ እጅግ ዘመንም በሕይወት ቢኖር፥ ዕድሜውም እጅግ ዓመት ቢሆን፥ ነገር ግን ነፍሱ መልካምን ነገር ባትጠግብ፥ መቃብርንም ባያገኝ፥ ከእርሱ ይልቅ ጭንጋፍ ይሻላል አልሁ።
4
በከንቱ መጥቷል በጨለማ ይሄዳል ስሙም በጨለማ ይሸፈናል፥
5
ደግሞም ፀሐይን አላየውም አላወቀውምም፥ ቢሆንም እርሱ ከዚያ ይልቅ ዕረፍት አለው።
6
ለሺህ ዓመት ሁለት ጊዜ በሕይወት ቢኖር፥ ነገር ግን መልካምን ባያይ፥ ሁሉም ወደ አንድ ስፍራ ይሄድ የለምን?
7
የሰው ድካም ሁሉ ለአፉ ነው፥ ነፍሱ ግን አትጠግብም።
8
ጥበበኛ ከአላዋቂ ምን የተሻለ ጥቅም ያገኛል? ሕይወትን መምራት የሚያውቅ ድሀስ ምን ይጠቀማል?
9
በዐይን ማየት በምኞት ከመቅበዝበዝ ይሻላል፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።
10
የሆነው ነገር በሙሉ ስሙ አስቀድሞ ተጠርቷል፥ ሰውም ማን እንደሆነ ታወቀ፥ ከእርሱ ከሚበረታው ጋር መፋረድ አይችልም።
11
ንግግር በበዛ መጠን፥ ከንቱነትም ይበዛል፤ ለሰውስ ምን ይጠቅመዋል?
12
ሰው በከንቱ የሕይወቱ ቀናት ቍጥር ና እንደ ጥላ በሚያሳልፈው ዘመኑ በሕይወቱ ሳለ ለሰው የሚሻለውን የሚያውቅ ማነው? ወይስ ከፀሐይ በታች ከእርሱ በኋላ የሚሆነውን ለሰው ማን ይነግረዋል?
← Chapter 5
Chapter 7 →