bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
2 Chronicles 36
2 Chronicles 36
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
የአገሩም ሰዎች የኢዮስያስን ልጅ ኢዮአክስን ወስደው በአባቱ ፋንታ በኢየሩሳሌም አነገሡት።
2
ኢዮአክስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ ሦስት ዓመት ጎልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ሦስት ወር ነገሠ።
3
የግብጽም ንጉሥ ከኢየሩሳሌም ከመንግሥቱ አወረደው፥ በምድሪቱም በሚኖሩት ላይ መቶ መክሊት ብርና አንድ መክሊት ወርቅ ግብር ጣለባቸው።
4
የግብጽም ንጉሥ ወንድሙን ኤልያቄምን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠ፥ ስሙንም ኢዮአቄም ብሎ ለወጠው፤ ኒካዑም ወንድሙን ኢዮአክስን ይዞ ወደ ግብጽ ወሰደው።
5
ኢዮአቄምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ አምስት ዓመት ጎልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ በአምላኩም በጌታ ፊት ክፉ አደረገ።
6
የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደናፆር በኢዮአቄም ላይ መጣበት፤ እርሱንም ወደ ባቢሎን ለመውሰድ በሰንሰለት አሰረው።
7
ናቡከደናፆርም ከጌታ ቤት ዕቃ አያሌውን ወደ ባቢሎን አጋዘ፥ በባቢሎንም በመቅደሱ ውስጥ አኖረው።
8
የቀረውም የኢዮአቄም ነገር፥ ያደረገውም ርኩሰት፥ በእርሱም የተገኘው ሁሉ፥ እነሆ፥ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፎአል፤ ልጁም ዮአኪን በእርሱ ፋንታ ነገሠ።
9
ዮአኪንም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የስምንት ዓመት ልጅ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ሦስት ወርና ዐሥር ቀን ነገሠ፤ በጌታም ፊት ክፉ አደረገ።
10
ዓመቱ ባለፈ ጊዜ ንጉሡ ናቡከደናፆር ልኮ ወደ ባቢሎን ወሰደው፥ የከበረውንም የጌታን ቤት ዕቃ ከእርሱ ጋር አስወሰደ፤ ወንድሙንም ሴዴቅያስን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠ።
11
ሴዴቅያስ መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ አንድ ዓመት ጎልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ።
12
በአምላኩም በጌታ ፊት ክፉ አደረገ፤ ከጌታም አንደበት የመጣውን ቃል በተናገረው በነቢዩ በኤርምያስ ፊት ራሱን አላወረደም።
13
ደግሞም በጌታ አምሎት በነበረው በንጉሡ በናቡከደናፆር ላይ ዓመፀ፤ ወደ እስራኤልም አምላክ ወደ ጌታ እንዳይመለስ አንገቱን አደነደነ ልቡንም አጠነከረ።
14
ደግሞም የካህናቱ አለቆች ሁሉ ሕዝቡም እንደ አሕዛብ ያለ ርኩሰት ሁሉ በመከተል መተላለፍን አበዙ፤ በኢየሩሳሌምም ጌታ ራሱ የቀደሰውን የጌታን ቤት አረከሱ።
15
የአባቶቻቸውም አምላክ ጌታ ለሕዝቡና ለማደሪያው ስላዘነ ማለዳ ተነሥቶ መልክተኞቹን ወደ እነርሱ ይልክ ነበር።
16
እነርሱ ግን የጌታ ቁጣ በሕዝቡ ላይ እስኪወርድባቸው ድረስ፥ ፈውስም እስከማይገኝላቸው ድረስ፥ በጌታ መልክተኞች ይሳለቁ፥ ቃላቱንም ያቃልሉ፥ በነቢያቱም ላይ ያፌዙ ነበር።
17
ስለዚህም የከለዳውያንን ንጉሥ አመጣባቸው፤ እርሱም ጉልማሶቻቸውን በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሰይፍ ገደላቸው፤ ጎልማሳውንና ድንግሊቱን ሽማግሌውንና አዛውንቱን አልማረም፤ ሁሉንም በእጁ አሳልፎ ሰጠው።
18
የእግዚአብሔርንም ቤት ዕቃ ሁሉ፥ ታላቁንና ታናሹን፥ የጌታንም ቤት መዝገብ፥ የንጉሡንና የሹማምንቱን መዝገብ፥ እነዚህን ሁሉ ወደ ባቢሎን ወሰደ።
19
የእግዚአብሔርንም ቤት አቃጠሉ፥ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር አፈረሱ፥ የንጉሥ ቅጥሮችዋንም ሁሉ በእሳት አቃጠሉ፥ ዕንቊውንም ዕቃዋን ሁሉ አጠፉ።
20
ከሰይፍም ያመለጡትን ወደ ባቢሎን ማረካቸው፤ የፋርስ ንጉሥም እስኪነግሥ ድረስ ለንጉሡና ለልጆቹ ባርያዎች ሆኑ፤
21
በኤርምያስ አንደበት የተናገረው የጌታ ቃል እንዲፈጸም፥ ምድሪቱ ሰንበትን በማድረግዋ እስክታርፍ ድረስ፤ በተፈታችበትም ዘመን ሁሉ፥ ሰባ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ፥ ሰንበትን አደረገች።
22
በኤርምያስም አንደበት የተነገረው የጌታ ቃል እንዲፈጸም በፋርስ ንጉሥ በቂሮስ በመጀመሪያው ዓመት ጌታ የፋርስን ንጉሥ የቂሮስን መንፈስ አስነሣ፤ እርሱም በመንግሥቱ ሁሉ አዋጅ ነገረ፥ ደግሞም በጽሑፍ እንዲህ ብሎ አወጀ፦
23
“የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዲህ ይላል፦ ‘የሰማይ አምላክ ጌታ የምድርን መንግሥታት ሁሉ ሰጥቶኛል፤ በይሁዳም ባለችው በኢየሩሳሌም ቤት እንድሠራለት አዝዞኛል ከሕዝቡ ሁሉ በእናንተ ዘንድ ማንም ቢሆን አምላኩ ጌታ ከእርሱ ጋር ይሁን፥ እርሱም ይውጣ።’ ”
← Chapter 35