bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
1 Samuel 27
1 Samuel 27
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
ዳዊት በልቡ፦ “ከእነዚህ ቀናት በአንዱ በሳኦል እጅ መገደሌ ስለማይቀር፥ የሚበጀኝ ወደ ፍልስጥኤማውያን ምድር መሸሽ ብቻ ነው፤ ከዚያ በኋላም ሳኦል በእስራኤል ሁሉ እኔን ማሳደዱን ይተዋል፤ እኔም ከእጁ አመልጣለሁ” ብሎ አሰበ።
2
ስለዚህ ዳዊትና አብረውት ያሉት ስድስት መቶ ሰዎች ተነሥተው የጋት ንጉሥ ወደ ሆነው ወደ ማዖክ ልጅ ወደ አኪሽ ሄዱ።
3
ዳዊትና ሰዎቹ በጋት በአኪሽ ዘንድ ተቀመጡ፤ እያንዳንዱ ሰው ከቤተሰቡ ጋር ነበረ፤ ዳዊትም ከሁለቱ ሚስቶቹ ጋር፥ ከኢይዝራኤላዊቷ ከአሒኖዓም እና የናባል ሚስት ከነበረችው ከቀርሜሎሳዊቷ አቢጌል ጋር ነበር።
4
ሳኦልም፥ ዳዊት ወደ ጋት እንደ ሸሸ በሰማ ጊዜ፥ እርሱን ማሳደዱን ተወ።
5
ከዚያም ዳዊት አኪሽን፥ “በፊትህ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ፥ በአገሪቱ ካሉት ከተሞች በአንዲቱ እኖር ዘንድ ስፍራ ይሰጠኝ፤ ስለምን አገልጋይህ ካንተ ጋር በንጉሥ ከተማ ይቀመጣል?” አለው።
6
ስለዚህ በዚያ ዕለት አኪሽ ጺቅላግን ከተማ ሰጠው፤ ጺቅላግም ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የይሁዳ ነገሥታት ይዞታ ሆነች።
7
ዳዊት በፍልስጥኤማውያን ምድር አንድ ዓመት ከአራት ወር ተቀመጠ።
8
በዚያ ጊዜም ዳዊትና ሰዎቹ ወጥተው ጌሪሹራውያንን፥ ጌዛውያንንና አማሌቃውያንን ወረሩ። እነዚህ ሕዝቦች ከጥንት ጀምሮ፥ እስከ ሱርና እስከ ግብጽ ባለው ምድር ላይ ይኖሩ ነበር።
9
ዳዊትም ምድሪቱን በመታበት ጊዜ፥ ወንድም ሆነ ሴት በሕይወት አላስቀረም፤ በጎችንና ላሞችን፥ አህዮችንና ግመሎችን እንዲሁም ልብሶችን ወሰደ፤ ወደ አኪሽም ይዞ ተመለሰ።
10
አኪሽም፥ “ዛሬ በማን ላይ ዘመታችሁ?” ሲል በጠየቀው ጊዜ ዳዊት፥ “የዘመትነው በይሁዳ፥ ወይም በይራሕመኤላውያን፥ ወይም በቄናውያን ላይ ነው” እያለ ይመልስለት ነበር።
11
ዳዊት “ ‘እርሱ እንዲህ አድርጓል’ ብለው ይነግሩብናል” ብሎ ስላሰበ፥ ወንድም ሆነ ሴት በሕይወት አስቀርቶ ወደ ጋት አላመጣም። በፍልስጥኤም ግዛት በኖረበት ዘመን ሁሉ እንዲህ ማድረጉ የተለመደ ነበር።
12
አኪሽም በልቡ፥ “እርሱ ራሱ የገዛ ሕዝቡ የሆኑት እስራኤላውያን እጅግ እንዲጠሉት ስላደረገ፥ ለዘለዓለም አገልጋዬ ይሆናል” ብሎ ስላሰበ ዳዊትን አመነው።
← Chapter 26
Chapter 28 →