bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
1 Corinthians 16
1 Corinthians 16
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
አሁን ደግሞ ለቅዱሳን የሚደረገውን የገንዘብ መዋጮ በተመለከተ ለገላትያ አብያተ ክርስቲያናት በሰጠሁት መመሪያ መሠረት አድርጉ።
2
እኔ በምመጣበት ጊዜ የገንዘብ መዋጮ እንዳይደረግ፤ ከእናንተ እያንዳንዱ እንደገቢው መጠን በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን እየለየ ያስቀምጥ፤
3
እኔ ስመጣ እናንተ ለመረጣችኋቸው ሰዎች የመሸኛ ደብዳቤ ሰጥቼ ስጦታችሁን ወደ ኢየሩሳሌም እንዲያደርሱ እልካቸዋለሁ።
4
የእኔ መሄድ የሚያስፈልግ ከሆነ አብረውኝ ይሄዳሉ።
5
በመቄዶንያ በኩል ለመሄድ ስላቀድኩ በዚያ ሳልፍ ወደ እናንተ እመጣለሁ።
6
ወደምሄድበት ወደ ማናቸውም ስፍራ በጉዞዬ እንድትረዱኝ፥ እናንተ ጋር እቆይ ይሆናል፤ ምናልባትም ክረምቱን ከእናንተ ጋር እሰነብት ይሆናል።
7
አሁን እግረ መንገዴን ሳልፍ ልጐበኛችሁ አልፈልግም፤ ጌታ ቢፈቅድ ረዘም ላለ ጊዜ እናንተ ዘንድ ለመሰንበት ተስፋ አደርጋለሁ።
8
ነገር ግን እስከ በዓለ ኀምሳ በኤፌሶን እቆያለሁ፤
9
ምክንያቱም ታላቅ የሥራ በር ተከፍቶልኛል፤ ተቃዋሚዎችም ብዙ ናቸው።
10
ጢሞቴዎስ ወደ እናንተ ከመጣ፥ እርሱም እንደ እኔ የጌታን ሥራ የሚሠራ ነውና፥ አብሮአችሁ ያለ ሥጋት እንዲቀመጥ አድርጉ።
11
ስለዚህ ማንም አይናቀው፤ በሰላም ወደ እኔ እንዲመለስ እርዱት፤ መመለሱንም ከወንድሞች ጋር እየጠበቅን ነው።
12
ስለ ወንድማችን ስለ አጵሎስ ደግሞ፥ ከወንድሞች ጋር ወደ እናንተ እንዲመጣ አጥብቄ ለምኜው ነበር፤ እርሱ ግን አሁን ለመምጣት አልፈለገም፤ ሲመቸው ግን ይመጣል።
13
ንቁ፤ በእምነት ጽኑ፤ በርቱ፤ ጠንክሩ፤
14
የምታደርጉትን ሁሉ በፍቅር አድርጉ።
15
ወንድሞች ሆይ፥ የእስጢፋኖስ ቤተሰቦች በአካይያ የመጀመሪያዎቹ አማኞች እንደሆኑና ቅዱሳንንም ለማገልገል ራሳቸውን እንደሰጡ ታውቃላችሁ።
16
እንደ እነርሱ ላሉትና ከእነርሱም ጋር በአገልግሎት ለሚደክሙ ሁሉ ታዘዙ።
17
በእስጢፋኖስ፥ በፈርዶናጥስና በአካይቆስ መምጣት ደስ ብሎኛል፤ ምክንያቱም እናንተ እዚህ ባለመኖራችሁ የጐደለኝን አሟልተዋል፤
18
የእኔንም የእናንተንም መንፈስ አሳርፈዋታልና። እንደነዚህ ያሉት ሰዎች እውቅና ይገባቸዋል።
19
በእስያ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። አቂላና ጵርስቅላ፥ በቤታቸውም ያለችው ቤተ ክርስቲያን የከበረ ሰላምታ በጌታ ያቀርቡላችኋል።
20
ወንድሞች ሁሉ ሰላምታ ያቅርቡላችኋል። እርስ በርሳችሁ በተቀደሰ አሳሳም ሰላምታ ተሰጣጡ።
21
እኔ ጳውሎስ፥ ይህን ሰላምታ በገዛ እጄ ጽፌላችኋለሁ።
22
ጌታን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን። ጌታችን ሆይ! ና!
23
የጌታ ኢየሱስ ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።
24
ፍቅሬ በክርስቶስ ኢየሱስ ከሁላችሁ ጋር ይሁን፤ አሜን።
← Chapter 15