bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
/
1 Chronicles 13
1 Chronicles 13
Amharic Catholic Version (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)) No Year
1
ዳዊትም ከሻለቆችና ከመቶ አለቆች ከሹማምንቱም ሁሉ ጋር ተማከረ።
2
ዳዊትም የእስራኤልን ጉባኤ ሁሉ እንዲህ አላቸው፦ “መልካም መስሎ ቢታያችሁ፥ የጌታም የአምላካችን ፈቃድ ቢሆን፥ በእስራኤል አገር ሁሉ ለቀሩት ወንድሞቻችን በከተሞቻቸውና በመሰማሪያዎቻቸውም ለተቀመጡት ካህናትና ሌዋውያን ወደ እኛ እንዲሰበሰቡ እንላክባቸው፤
3
በሳኦልም ዘመን አልፈለግነውምና የአምላካችንን ታቦት ወደ እኛ እንመልስ።”
4
ነገሩም በሕዝቡ ሁሉ ዐይን ዘንድ ቅን ነበረና ጉባኤው ሁሉ፦ “እንዲሁ እናደርጋለን” አሉ።
5
የእግዚአብሔርንም ታቦት ከቂርያት-ይዓሪም ለማምጣት ዳዊት እስራኤልን ሁሉ ከግብጽ ወንዝ ከሺሆር ጀምሮ እስከ ሐማት መግቢያ ድረስ ሰበሰበ።
6
ዳዊትም እስራኤልም ሁሉ በኪሩቤል ላይ የተቀመጠውን ስሙም በእርሱ የተጠራውን የጌታን የእግዚአብሔርን ታቦት ከዚያ ለማምጣት በይሁዳ ወዳለችው ቂርያት-ይዓሪም ወደተባለች ወደ በኣላ ሄዱ።
7
የእግዚአብሔርንም ታቦት በአዲስ ሠረገላ ላይ ጫኑት፥ ከአሚናዳብም ቤት አመጡት፤ ዖዛና አሒዮም ሠረገላውን ይነዱ ነበር።
8
ዳዊትና እስራኤል ሁሉ በዝማሬና በበገና በመሰንቆና በከበሮ በጸናጸልና በመለከት በእግዚአብሔር ፊት በሙሉ ኃይላቸው ያሸበሽቡ ነበር።
9
ወደ ኪዶንም አውድማ በደረሱ ጊዜ በሬዎቹ ይፋንኑ ነበርና ታቦቱን ሊይዝ ዖዛ እጁን ዘረጋ።
10
የጌታም ቁጣ በዖዛ ላይ ነደደ፥ እጁንም ወደ ታቦቱ ስለዘረጋ ቀሠፈው፤ በዚያም በእግዚአብሔር ፊት ሞተ።
11
ጌታም ዖዛን ስለ ቀሠፈው ዳዊት አዘነ፤ እስከ ዛሬም ድረስ የዚያን ስፍራ ስም የዖዛ-ስብራት ብሎ ጠራው።
12
በዚያም ቀን ዳዊት፦ “የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ እኔ እንዴት አመጣለሁ?” ብሎ እግዚአብሔርን ፈራ።
13
ዳዊትም ታቦቱን ወደ ጌት ሰው ወደ አቢ-ዳራ ቤት ወሰደው እንጂ ወደ እርሱ ወደ ዳዊት ከተማ አላመጣውም።
14
የእግዚአብሔርም ታቦት በአቢ-ዳራ ቤተሰብ ዘንድ በቤቱ ውስጥ ሦስት ወር ተቀመጠ፤ ጌታም የአቢ-ዳራን ቤትና ያለውን ሁሉ ባረከ።
← Chapter 12
Chapter 14 →