bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Romans 13
Romans 13
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
ሰው ሁሉ በበላይ ላሉ ባለሥልጣኖች ይገዛ፤ ከእግዚአብሔር ከአልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው።
2
ለባለሥልጣን አልገዛም ያለ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንቢ ማለቱ ነው፤ መገዛትን እንቢ የሚሉም በራሳቸው ላይ ቅጣትን ያመጣሉ።
3
ሹሞች ሥራው ክፉ ለሆነ ሰው እንጂ መልካም ለሚሠራ የሚአስፈሩ አይደሉም፤ ሹሞችን እንዳትፈራ ብትፈልግ መልካም አድርግ፤ እነርሱ ደግሞ ያመሰግኑሃል፤
4
አንተ ሥራህን ታሳምር ዘንድ የእግዚአብሔር መልእክተኞች ናቸውና። ክፉ ብታደርግ ግን ፍራ፤ ሰይፍ የታጠቁም ለከንቱ አይደለም፤ ክፉ አድራጊዎችን ለመቅጣት የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸውና።
5
ስለዚህ ቍጣን ስለ መፍራት ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን ስለ ሕሊና ደግሞ መገዛት ግድ ነው።
6
ስለዚህም ግብር ታገቡላቸዋላችሁ፤ ለዚህ ሥራ የተሾሙ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸውና፤
7
ለሁሉም እንደሚገባው አድርጉ፤ ግብር ለሚገባው ግብርን ስጡ፤ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን ስጡ፤ ዐሥራት ለሚገባው ዐሥራትን ስጡ፤ ሊፈሩት የሚገባውን ፍሩ፤ ክብር የሚገባውንም አክብሩ።
8
እርስ በርሳችሁ ከመዋደድ በቀር ለማንም ዕዳ አይኑርባችሁ፤ ባልንጀራውን የወደደ ግን ሕግን ሁሉ ፈጸመ።
9
በኦሪት እንዲህ ብሎአልና፥ “አታመንዝር፤ አትግደል፤ አትስረቅ፤ በሐሰት አትመስክር፥ አትመኝ፤” ደግሞ ሌላ ትእዛዝ አለ፤ ነገር ግን የሁሉም ራስ “ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ” የሚለው ነው።
10
ባልንጀራዉን የሚወድ በባልንጀራዉ ላይ ክፉ ሥራ አይሠራም፤ ስለዚህ ፍቅር የሕግ ፍጻሜ ነው።
11
ከእንቅልፍ የምትነቁበት ጊዜ እንደ ደረሰ ዕወቁ፤ ካመንበት ጊዜ ይልቅ መዳናችን ዛሬ ወደ እና ደርሳለችና።
12
ሌሊቱ አልፎአል፤ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማን ሥራ ከእና እናርቅ፤ የብርሃንንም ጋሻ ጦር እንልበስ።
13
በቀን እንደሚሆን በጽድቅ ሥራ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር፥ በዝሙትና በመዳራትም አይሁን፤ በክርክርና በቅናትም አይሁን።
14
ነገር ግን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ልበሱት፤ የሥጋችሁንም ምኞት አታስቡ።
← Chapter 12
Chapter 14 →