bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 81
Psalms 81
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
እግዚአብሔር በአማልክት ማኅበር ቆመ፥ በአማልክትም መካከል ይፈርዳል።
2
እስከ መቼ ዐመፃን ትፈርዳላችሁ? እስከ መቼስ ለኀጢአተኞች ፊት ታደላላችሁ?
3
ለድሆችና ለድሃ አደጎች ፍረዱ፤ ለተገፋውና ለምስኪኑ ጽድቅን አድርጉ፤
4
ብቸኛውንና ችግረኛውን አድኑ፤ ከኃጥኣንም እጅ አስጥሉአቸው።
5
አያውቁም፥ አያስተውሉምም፤ በጨለማ ውስጥም ይመላለሳሉ፤ የምድር መሠረቶች ሁሉ ተናወጡ።
6
እኔ ግን እላለሁ፥ “አማልክት ናችሁ፥ ሁላችሁም የልዑል ልጆች ናችሁ፤”
7
እናንተ ግን እንደ ሰው ትሞታላችሁ፥ ከአለቆችም እንደ አንዱ ትወድቃላችሁ።
8
አቤቱ፥ ተነሥ፥ በምድር ላይ ፍረድ፥ አንተ አሕዛብን ሁሉ ትወርሳለህና።
← Chapter 80
Chapter 82 →