bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 8
Psalms 8
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
አቤቱ ጌታችን፥ ስምህ በምድር ሁሉ እጅግ ተመሰገነ፥ ምስጋናህ በሰማዮች ላይ ከፍ ከፍ ብሎአልና።
2
ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ፥ ስለ ጠላት፥ ጠላትንና ግፈኛን ታጠፋው ዘንድ።
3
የጣቶችህን ሥራ ሰማዮችን፥ አንተ የሠራሃቸውን፥ ጨረቃንና ከዋክብትን እናያለንና።
4
ታስበው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ትጐበኘውም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው?
5
ከመላእክት ጥቂት አሳነስኸው፤ በክብርና በምስጋና ዘውድ ከለልኸው።
6
በእጆችህም ሥራ ሁሉ ላይ ሾምኸው፤ ሁሉን ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት፥
7
በጎችንም በሬዎችንም ሁሉ፥ ደግሞም የምድረ በዳውን እንስሶች፥
8
የሰማይንም ወፎች፥ የባሕርንም ዓሦች፥ በባሕር መንገድ የሚሄደውንም ሁሉ።
9
አቤቱ፥ ጌታችን፥ ስምህ በምድር ሁሉ እጅግ ተመሰገነ።
← Chapter 7
Chapter 9 →