bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 79
Psalms 79
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
ዮሴፍን እንደ መንጋ የምትመራ፥ የእስራኤል ጠባቂ ሆይ፥ አድምጥ፤ በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ፥ ተገለጥ።
2
በኤፍሬምና በብንያም በምናሴም ፊት ኀይልህን አንሣ፥ እኛንም ለማዳን ና።
3
የኀያላን አምላክ፥ መልሰን፥ ፊትህንም አብራ፥ እኛም እንድናለን።
4
የኀያላን አምላክ አቤቱ፥ በባሪያህ ጸሎት ላይ እስከ መቼ ትቈጣለህ?
5
የእንባችንን እንጀራ ትመግበናለህ፥ እንባችንንም በስፍር ታጠጣናለህ።
6
ለጎረቤቶቻችን መነጋገሪያ አደረግኸን፥ ጠላቶቻችንም በላያችን ተሳለቁብን።
7
የኀያላን አምላክ አቤቱ፥ መልሰን፥ ፊትህንም አብራ፥ እኛም እንድናለን።
8
ከግብፅ የወይንን ግንድ አመጣህ፤ አሕዛብን አባረርህ፥ እርስዋንም ተከልህ።
9
በፊቷም መንገድን ጠረግህ፥ ሥሮችዋንም ተከልህ፥ ምድርንም ሞላች።
10
ጥላዋ ተራሮችን ከደነ፥ ጫፎችዋም እንደ እግዚአብሔር ዝግባ ሆኑ።
11
ቅርንጫፎችዋንም እስከ ባሕር፥ ቡቃያዋንም እስከ ወንዙ ዘረጋች።
12
አጥርዋን ለምን አፈረስህ? መንገድ አላፊም ሁሉ ይበላታል።
13
የበረሃ እርያ አረከሳት፥ የዱር አውሬም ተሰማራባት።
14
የኀያላን አምላክ ሆይ፥ እባክህ ተመለስ፤ ከሰማይ ተመልከት፥ እይም፥ ይህችንም የወይን ግንድ ይቅር በላት።
15
በሰው ልጅ ለአንተ ያጸናኻትን ቀኝህ የተከላትን አጽንተህ አነሣሣት።
16
በእሳት ተቃጥላለች፥ ተነቅላማለች ከፊትህ ተግሣጽም የተነሣ ይጠፋሉ።
17
ለአንተ ባጸናኸው በሰው ልጅ ላይ፥ በቀኝህ ሰው ላይ እጅህ ይሁን።
18
ከአንተም አንራቅ፤ አድነን፥ ስምህንም እንጠራለን።
19
የኀያላን አምላክ አቤቱ፥ መልሰን፥ ፊትህንም አብራ፥ እኛም እንድናለን።
← Chapter 78
Chapter 80 →