bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 65
Psalms 65
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
በምድር ያላቸሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፥
2
ለስሙም ዘምሩ፥ ለክብሩም ምስጋናን ስጡ።
3
እግዚአብሔርን እንዲህ በሉት፥ “ሥራህ ግሩም ነው፤ ኀይልህ ብዙ ሲሆን ጠላቶችህ ዋሹብህ።”
4
ምድር ሁላ ለአንተ ትሰግዳለች፥ ለአንተም ትገዛለች፥ ለስምህም ትዘምራለች።
5
የእግዚአብሔርን ሥራ ታዩ ዘንድ ኑ። ምክሩ ከሰው ልጆች ይልቅ ግሩም ነው።
6
ባሕርን የብስ አደረጋት፥ ወንዙንም በእግር ተሻገሩ፤ በዚያ በእርሱ ደስ ይለናል።
7
በኀይሉ ለዘለዓለም ይገዛል፤ ዐይኖቹ ወደ አሕዛብ ይመለከታሉ፤ የምታውቁ ራሳችሁን ከፍ ከፍ አታድርጉ።
8
አሕዛብ ሆይ፥ አምላካችንን አመስግኑ፥ የምስጋናውንም ቃል አድምጡ።
9
ነፍሴን በሕይወት ያኖራታል፥ ለእግሮቼም ሁከትን አልሰጠም።
10
አቤቱ፥ ፈትነኸናልና፥ ብርንም እንደሚያነጥሩት አንጥረኸናልና።
11
ወደ ወጥመድም አገባኸን፥ በፊታችንም መከራን አመጣህ።
12
በራሳችን ላይ ሰውን አስጫንህ፤ በእሳትና በውኃ መካከል አሳለፍኸን፥ ወደ ዕረፍትም አወጣኸን።
13
መባዬን ይዤ ወደ ቤትህ እገባለሁ፤
14
በመከራዬ ጊዜ በአፌ የተናገርሁትን በከንፈሮቼም ያልሁትን ስእለቴን ለአንተ እሰጣለሁ።
15
ከዕጣንና ከሙክቶች ጋር ነውር የሌለበት ንጹሕ መሥዋዕትን አቀርብልሃለሁ፤ ላሞችንና ፍየሎችንም እሠዋልሃለሁ።
16
እግዚአብሔርን የምትፈሩት ሁሉ፥ ኑ፥ ስሙኝ፤ ለነፍሴ ያደረገላትን ልንገራችሁ።
17
በአፌ ወደ እርሱ ጮኽሁ፥ በአንደበቴም ከፍ ከፍ አደረግሁት።
18
በልቤስ በደልን አይቶ ቢሆን እግዚአብሔር አይሰማኝም ነበር።
19
ስለዚህ እግዚአብሔር ሰማኝ፤ የልመናዬንም ድምፅ አደመጠ።
20
ጸሎቴን ያልከለከለኝ፥ ምሕረቱንም ከእኔ ያላራቀ፥ እግዚአብሔር ይመስገን።
← Chapter 64
Chapter 66 →