bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 5
Psalms 5
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
አቤቱ፥ ቃሌን አድምጥ፥ ጩኸቴንም አስተውል፤
2
የልመናዬን ቃል አድምጥ፥ ንጉሤና አምላኬ ሆይ፥ አቤቱ፥ ወደ አንተ እጸልያለሁና።
3
በማለዳ ቃሌን ስማኝ፥ በማለዳ በፊትህ እቆማለሁ፥ እገለጥልሃለሁም።
4
አንተ በደልን የሚወድድ አምላክ አይደለህምና፤ ክፉዎች ከአንተ ጋር አያድሩም።
5
ዐመፀኞችም በዐይኖችህ ፊት አይኖሩም፤ ዐመፅ አድራጊዎችን ሁሉ ጠላህ።
6
ሐሰትን የሚናገሩትን ሁሉ ትጥላቸዋለህ፤ ደም አፍሳሹንና ሸንጋዩን ሰው እግዚአብሔር ይጸየፋል።
7
እኔ ግን በምሕረትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ፤ አንተን በመፍራት በቤተ መቅደስህ እሰግዳለሁ።
8
አቤቱ፥ በጽድቅህ ምራኝ፤ ስለ ጠላቶቼ መንገዴን በፊትህ አቅና።
9
በአፋቸው እውነት የለምና፥ ልባቸውም ከንቱ ነው፥ ጕሮሮኣቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸው ይሸነግላሉ።
10
አቤቱ፥ ፍረድባቸው፥ በነገረ ሠሪነታቸውም ይውደቁ፤ እንደ ሐሰታቸውም ብዛት አሳድዳቸው፥ አቤቱ፥ እነርሱ አሳዝነውሃልና።
11
በአንተ የሚታመኑት ሁሉ ግን ደስ ይላቸዋል፤ ለዘለዓለሙ ደስ ይላቸዋል፥ በእነርሱም ታድራለህ። ስምህንም የሚወድዱ ሁሉ በአንተ ይመካሉ።
12
አንተ ጻድቁን ትባርከዋለህና፤ አቤቱ፥ እንደ አላባሽ ጋሻ ከለልኸን።
← Chapter 4
Chapter 6 →