bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 41
Psalms 41
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
ዋሊያ ወደ ውኃ ምንጮች እንደሚናፍቅ፥ እንዲሁ ነፍሴ ወደ እግዚአብሔር ትናፍቃለች።
2
ነፍሴ ወደ ሕያው አምላኬ ተጠማች፤ መቼ እደርሳለሁ? የአምላኬንስ ፊት መቼ አያለሁ?
3
ዘወትር፥ “አምላክህ ወዴት ነው?” ይሉኛልና እንባዬ በቀንና በሌሊት ምግብ ሆነኝ።
4
ይህን ሳስብ ነፍሴ በእኔ ውስጥ ፈሰሰች፥ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ምስጋና መኖሪያ ስፍራ እገባለሁና፤ በዓልን የሚያደርጉ ሰዎች በምስጋናና በደስታ ቃል ሲያመሰግኑ ተሰሙ።
5
ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድኀኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሔር ታመኚ።
6
ነፍሴ በእኔ ውስጥ ታወከች፤ ስለዚህ አቤቱ በዮርዳኖስ ምድር፥ በአርሞንኤምም በታናሹ ተራራ አስብሃለሁ።
7
በፍዋፍዋቴህ ድምፅ ቀላይ ቀላይን ትጠራዋለች፤ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላዬ አለፈ።
8
እግዚአብሔር በቀን ይቅርታውን ያዝዛል፥ በሌሊትም እርሱን ይናገራል፤ ከእኔ ዘንድ የሕይወቴ ብፅዐት ለእግዚአብሔር ነው።
9
እግዚአብሔርን አልሁት፥ “አንተ አምላኬ ነህ፤ ለምን ረሳኸኝ? ጠላቶቼ ሲያስጨንቁኝ ለምን ተውኸኝ? ለምንስ አዝኜ እመለሳለሁ?” ጠላቶቼ ሁሉ አጥንቶቼን እየቀለጣጠሙ ሰደቡኝ።
10
ሁልጊዜ፥ “አምላክህ ወዴት ነው?” ይሉኛልና።
11
ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድኀኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሔር ታመኚ።
← Chapter 40
Chapter 42 →