bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 35
Psalms 35
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
ኀጢአተኛ ራሱን የሚያስትበትን ነገር ይናገራል፥ የእግዚአብሔርም ፍርሀት በዐይኖቹ ፊት የለም።
2
በአንደበቱ ሸንግሎአልና፤ ኀጢአቱ ባገኘችው ጊዜ ይጠላታል።
3
የአፉ ቃል ዐመፅና ሽንገላ ነው፤ በጎ ሥራን ይሠራ ዘንድ ማስተዋልን አልወደደም።
4
በመኝታው ዐመፅን ዐሰበ፤ በሁሉ ነገር መልካም ባልሆነች መንገድ ቆሞአል፤ ክፋትንም አይሰለቻትም።
5
አቤቱ፥ ምሕረትህ በሰማይ ነው፥ እውነትህም እስከ ደመናት ትደርሳለች።
6
ጽድቅህም እንደ እግዚአብሔር ተራሮች ናት፤ ፍርድህም እጅግ ጥልቅ ናት።
7
አቤቱ፥ ሰውንና እንስሳን ታድናለህ። አቤቱ፥ ምሕረትህን እንደ አበዛህ፥ የሰው ልጆች በክንፎችህ ጥላ ይታመናሉ።
8
ከቤትህ ጠል ይረካሉ። ከደስታህም ፈሳሽ ታጠጣቸዋለህ።
9
የሕይወት ምንጭ ከአንተ ዘንድ ነውና፤ በብርሃንህ ብርሃንን እናያለን።
10
ምሕረትህን በሚያውቁህ ላይ፥ ጽድቅህንም በልበ ቅኖች ላይ ዘርጋ።
11
የትዕቢት እግር አይምጣብኝ፥ የኀጢአተኛ እጅም አያውከኝ።
12
ዐመፃን የሚያደርጉ ሁሉ በዚያ ይወድቃሉ፤ ይሰደዳሉ፥ መቆምም አይችሉም።
← Chapter 34
Chapter 36 →