bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 32
Psalms 32
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
ጻድቃን ሆይ፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ ለቅኖችም ክብር ይገባል።
2
እግዚአብሔርንም በመሰንቆ አመስግኑት፥ ዐሥር አውታርም ባለው በገና ዘምሩለት።
3
አዲስ ምስጋናንም አመስግኑት፥ በእልልታም መልካም ዝማሬ ዘምሩለት፤
4
የእግዚአብሔር ቃል እውነት ነውና ሥራውም ሁሉ በእምነት ነውና።
5
እግዚአብሔር ጽድቅንና ምጽዋትን ይወድዳል፤ የእግዚአብሔር ይቅርታው ምድርን ሞላ።
6
በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ፥ ሠራዊታቸውም ሁሉ በአፉ እስትንፋስ፤
7
የባሕሩን ውኃ እንደ ረዋት የሚሰበስበው፥ በቀላዮችም መዝገቦች የሚያኖረው።
8
ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን ትፈራዋለች፥ በዓለም የሚኖሩ ሁሉም ከእርሱ የተነሣ ይደነግጣሉ።
9
እርሱ ተናግሮአልና፥ ሆኑ፤ እርሱ አዘዘ፤ ተፈጠሩም።
10
እግዚአብሔር የአሕዛብን ምክር ይመልሳል፥ የሕዝቡንም ዐሳብ ይመልሳል። የአለቆችን ምክራቸውን ያስረሳቸዋል።
11
የእግዚአብሔር ምክር ግን ለዘለዓለም ይኖራል፥ የልቡም ዐሳብ ለልጅ ልጅ ነው።
12
እግዚአብሔር አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ብፁዕ ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።
13
እግዚአብሔር ከሰማይ ተመለከተ፥ የሰውንም ልጆች ሁሉ አየ።
14
ከተዘጋጀው የመቅደሱ አዳራሽ ሆኖ በምድር ወደሚኖሩ ሁሉ ተመለከተ፤
15
እርሱ ብቻውን ልባቸውን የሠራ፥ ሥራቸውንም ሁሉ የሚያውቅ እርሱ ነው።
16
ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት አይድንም፥ ኀያልም በኀይሉ ብዛት አይድንም።
17
ፈረስም ከንቱ ነው፥ አያድንም፤ በኀይሉም ብዛት አያመልጥም።
18
እነሆ፥ የእግዚአብሔር ዐይኖች ወደሚፈሩት ናቸው፤ በምሕረቱም ወደሚታመኑ፥
19
ነፍሳቸውን ከሞት ያድናታል፥ በራብም ጊዜ ይመግባቸዋል።
20
ነፍሳችን እግዚአብሔርን ተስፋ ታደርገዋለች፥ ረዳታችንና መጠጊያችን እርሱ ነውና።
21
ልባችን በእርሱ ደስ ይለዋልና፥ በቅዱስ ስሙም ታምነናልና።
22
አቤቱ፥ በአንተ እንደ ታመንን፥ ምሕረትህ በላያችን ትሁን።
← Chapter 31
Chapter 33 →