bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 134
Psalms 134
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
የእግዚአብሔርን ስም አመስግኑ፤ እናንተ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሆይ፥ አመስግኑት።
2
በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ፥ በአምላካችን ቤት አደባባይ የምትቆሙ።
3
እግዚአብሔር ቸር ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ለስሙ ዘምሩ፥ መልካም ነውና፤
4
እግዚአብሔር ያዕቆብን ለራሱ፥ እስራኤልንም ርስቱ እንዲሆን መርጦታልና፤
5
እግዚአብሔር ታላቅ እንደ ሆነ፥ አምላካችንም ከአማልክት ሁሉ እንዲበልጥ አውቃለሁና።
6
በሰማይና በምድር፥ በባሕርና በጥልቆችም ሁሉ፥ እግዚአብሔር የወደደውን ሁሉ አደረገ።
7
ከምድር ዳር ደመናትን ያወጣል፤ ለዝናም ጊዜም መብረቅን አደረገ፤ ነፋሳትንም ከመዛግብቱ ያወጣል።
8
የግብፅን በኵር ልጆች ሁሉ ከሰው ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ገደለ።
9
ግብፅ ሆይ፥ በመካከልሽ በፈርዖንና በባሪያዎቹ ሁሉ ላይ ተአምራትንና ድንቅን ሰደደ።
10
ብዙ አሕዛብን መታ፥ ብርቱዎችንም ነገሥታት ገደለ።
11
የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን፥ የባሳንንም ንጉሥ ዐግን፥ የከነዓንን ነገሥታት ሁሉ ገደለ፤
12
ርስት ምድራቸውንም ለሕዝቡ ለእስራኤል ርስት አድርጎ ሰጠ።
13
አቤቱ፥ ስምህ ለዘለዓለም ነው፥ መታሰቢያህም ለልጅ ልጅ ነው፤
14
እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይፈርዳልና፥ ባሪያዎቹንም ያጽናናልና።
15
የአሕዛብ ጣዖታት የብርና የወርቅ፥ የሰው እጅ ሥራ ናቸው።
16
አፍ አላቸው፥ ግን አይናገሩም፤ ዐይን አላቸው፥ ግን አያዩም፤
17
ጆሮ አላቸው፥ ግን አይሰሙም፤ አፍንጫ አላቸው፥ ግን አያሸቱም፤ እጅ አላቸው፥ ግን አይዳስሱም፤ እግር አላቸው፥ ግን አይሄዱም፤ በጕሮሮአቸው አይናገሩም፥ እስትንፋስም በአፋቸው የለም።
18
የሚሠሩአቸው ሁሉ፥ የሚታመኑባቸውም ሁሉ እንደ እነርሱ ይሁኑ።
19
የእስራኤል ወገኖች ሆይ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑት፤ የአሮን ወገኖች ሆይ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑት፤
20
የሌዊ ወገኖች ሆይ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑት፤ እግዚአብሔርን የምትፈሩት ሆይ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑት።
21
በኢየሩሳሌም የሚያድር እግዚአብሔር በጽዮን የተመሰገነ ነው።
← Chapter 133
Chapter 135 →