bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 102
Psalms 102
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
ነፍሴ፥ እግዚአብሔርን ታመሰግነዋለች። አጥንቶቼም ሁሉ የተቀደሰ ስሙን።
2
ነፍሴ እግዚአብሔርን ታመሰግነዋለች፥ ምስጋናውንም ሁሉ አትረሳም።
3
ኀጢአትህን ሁሉ ይቅር የሚልልህ፤ ደዌህንም ሁሉ የሚፈውስህ፥
4
ሕይወትህን ከጥፋት የሚያድናት፥ በይቅርታውና በምሕረቱ የሚከልልህ፥
5
ምኞትህን ከበረከቱ የሚያጠግባት፥ ጐልማስነትህን እንደ ንስር የሚያድሳት፥
6
እግዝአብሔር ይቅርታ አድራጊ ነው፤ ለተበደሉ ሁሉ ይፈርዳል።
7
ለሙሴ መንገዱን አሳየ፥ ለእስራኤል ልጆችም ፈቃዱን።
8
እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ ነው፥ ከቍጣ የራቀ ምሕረቱም የበዛ ጻድቅ ነው።
9
ሁልጊዜም አይቀሥፍም፥ ለዘለዓለምም አይቈጣም።
10
እንደ ኀጢአታችን አላደረገብንም፥ እንደ በደላችንም አልከፈለንም።
11
ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ እግዚአብሔር ምሕረቱን በሚፈሩት ላይ አጸና።
12
ምሥራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅ፥ እንዲሁ ኀጢአታችንን ከእኛ አራቀ።
13
አባት ለልጆቹ እንደሚራራ፥ እንዲሁ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ይራራላቸዋል፤
14
ፍጥረታችንን እርሱ ያውቃልና፤ አቤቱ፥ እኛ አፈር እንደ ሆንን አስብ።
15
ሰውስ በዘመኑ እንደ ሣር ነው፤ እንደ ዱር አበባ እንዲሁ ያብባል፤
16
ነፍሱ ከእርሱ ይወጣልና፥ ከእንግዲህም ወዲህ አይኖርምና ስፍራውንም ደግሞ አያውቀውምና።
17
የእግዚአብሔር ይቅርታው ግን ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም በሚፈሩት ላይ፥ ጽድቁም በልጅ ልጆች ላይ ነው፤
18
ሕጉን በሚጠብቁ፥ ትእዛዙንም ያደርጉ ዘንድ በሚያስቡ ላይ ነው።
19
እግዚአብሔር ዙፋኑን በሰማይ አዘጋጀ፥ በመንግሥቱም ሁሉን ይገዛል።
20
ቃሉን የምትፈጽሙ፥ ብርቱዎችና ኀያላን፥ የቃሉንም ድምፅ የምትሰሙ መላእክቱ ሁሉ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑት፤
21
ሠራዊቱ ሁሉ፥ ፈቃዱን የሚያደርጉ አገልጋዮቹ፥ እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል።
22
ፍጥረቶቹ ሁሉ በግዛቱ ስፍራ ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል። ነፍሴ እግዚአብሔርን ታመሰግነዋለች።
← Chapter 101
Chapter 103 →