bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Psalms 100
Psalms 100
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
አቤቱ፥ ምሕረትንና ፍርድን እዘምርልሃለሁ።
2
እዘምራለሁ፥ ንጹሕ መንገድንም አስተውላለሁ፤ ወደ እኔ መቼ ትመጣለህ? በቤቴ መካከል በልቤ ቅንነት እሄዳለሁ።
3
በዐይኔ ፊት ክፉ ነገርን አላኖርሁም፤ ዐመፃ የሚያደርጉትን ጠላሁ።
4
ጠማማ ልብም አልተከተለኝም፤ ክፉ ከእኔ በራቀ ጊዜ አላወቅሁም።
5
ባልንጀራውን በስውር የሚያማን እርሱን አሳደድሁ፤ በዐይኑ ትዕቢተኛ የሆነውና ልቡ የሚሳሳው ከእኔ ጋር አይተባበርም።
6
ከእኔ ጋር አኖራቸው ዘንድ ዐይኖቼ ወደ ምድር ምእመናን ናቸው፤ በንጹሕ መንገድ የሚሄድ እርሱ ያገለግለኛል።
7
ትዕቢትን የሚያደርግ በቤቴ መካከል አይኖርም፥ ዐመፃን የሚናገር በፊቴ አይጸናም።
8
ዐመፃን የሚያደርጉትን ሁሉ ከእግዚአብሔር ከተማ አጠፋቸው ዘንድ፥ የምድርን ኀጢአተኞች ሁሉ በማለዳ እገድላቸዋለሁ።
← Chapter 99
Chapter 101 →