bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Proverbs 18
Proverbs 18
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
ከወዳጆቹ መለየትን የሚወድድ ሰው ምክንያትን ይፈልጋል፥ ሁልጊዜም ለሽሙጥ ይሆናል።
2
የዕውቀት ድሃ ጥበብን አይወድድም፤ ነገር ግን ስንፍና ይገዛዋል።
3
ኀጢአተኛ ወደ ጥፋት ጥልቅ በመጣ ጊዜ ቸል ይላል፥ ውርደትና ሽሙጥም በላዩ ይመጣል።
4
ቃል በብልህ ሰው ልብ ውስጥ የጠለቀ ውኃ ነው፥ የሚፈልቅም የሕይወት ምንጭና ፈሳሽ ወንዝ ነው።
5
የኃጥኣንን ፊት ማድነቅ መልካም አይደለም። በፍርድ ጊዜም እውነትን ማራቅ መልካም አይደለም፥
6
አላዋቂን ከንፈሮቹ ወደ ክፉ ያደርሱታል፥ የችኩል አፍም ሞትን ይጠራል።
7
የአላዋቂ አፍ ለራሱ ጥፋት ነው፥ ከንፈሮቹም ለነፍሱ ወጥመድ ናቸው።
8
ፍርሀት ሰነፎችን ይጥላል፥ የተቸገሩ ሰዎች ሰውነትም ይራባል።
9
በሥራው ራሱን የማያድን፥ ራሱን ለሚያጠፋ ወንድም ነው።
10
የእግዚአብሔር ስም ታላቅ ኀይል ነው፤ ጻድቃንም እርሱን በመከተል ከፍ ከፍ ይላሉ።
11
የባለጠጋ ሰው ሀብቱ የጸናች ከተማ ናት፥ ክብሯም እንደ ትልቅ ጥላ ታጠላለች።
12
ከመውደቅ በፊት የሰው ልቡ ከፍ ከፍ ይላል፥ ሳይከብርም ይዋረዳል።
13
ሳይሰማ ነገርን የሚመልስ ስንፍናና እፍረት ይሆንበታል።
14
ብልህ አገልጋይ የጌታውን ቍጣ ያበርዳል፥ አእምሮ የጐደለውን ሰው ማን ይችለዋል?
15
የብልህ ልብ ዕውቀትን ገንዘብ ያደርጋል፥ የጠቢባን ጆሮም ዕውቀትን ትፈልጋለች።
16
ሀብት ሰውን ከፍ ከፍ ያደርጋል፥ ከመኳንንት ጋርም ያኖረዋል።
17
ከፍርድ በፊት ራሱን የሚከስስ ጻድቅ ነው፥ ያመጣው ባላጋራውም ይገሠጻል።
18
ዕጣ ክርክርን ያስተዋል፥ በኀያላንም መካከል ይለያል።
19
ወንድሙን የሚረዳ ወንድም እንደ ጸናችና ከፍ እንዳለች ከተማ ነው። በጽኑ መሠረትም እንደ ታነጸ ሕንጻ የጸና ነው።
20
ሰው ሆዱን ከአፉ ፍሬ ይሞላል፥ ከከንፈሩም ፍሬ ይጠግባል።
21
ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው፤ የሚያጸኑአትም ፍሬዋን ይበላሉ።
22
ደግ ሚስትን ያገኘ ሞገስን አገኘ፥ ከእግዚአብሔርም ደስታን ተቀበለ። ደግ ሴትን የፈታ ደስታን አጣ፥ አመንዝራዪቱንም የሚያኖር አላዋቂና ኀጢአተኛ ነው።
← Chapter 17
Chapter 19 →