bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Luke 10
Luke 10
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
ከዚህም በኋላ ጌታችን ሌሎች ሰባ ሰዎችን መረጠ፤ ሁለት ሁለት አድርጎም ሊሄድበት ወደ አለው ከተማና መንደር በፊቱ ላካቸው።
2
ጌታችን ኢየሱስም አላቸው፥ “መከሩ ብዙ ነው፤ ሠራተኛው ግን ጥቂት ነው፤ እንግዲህ ለመከሩ ሠራተኛ ጨምሮ ይልክ ዘንድ ባለ መከሩን ለምኑት።
3
ሂዱ፤ እነሆ፥ እኔ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ።
4
ከረጢትም፥ ስልቻም፥ ጫማም፥ ምንም ምን አትያዙ፤ በመንገድም ማንንም ሰላም አትበሉ።
5
ወደ ገባችሁበት ቤትም አስቀድማችሁ ‘ለዚህ ቤት ሰዎች ሰላም ይሁን’ በሉ።
6
በዚያም የሰላም ልጅ ቢኖር ሰላማችሁ ያድርበታል፤ ያለዚያ ግን ሰላማችሁ ይመለስላችኋል።
7
በዚያም ቤት ተቀመጡ፤ ከእነርሱ የተገኘውንም ብሉ፥ ጠጡም፤ ለሠራተኛ ዋጋው ይገባዋልና፤ ከቤትም ወደ ቤት አትሂዱ።
8
ወደ ማናቸውም ከተማ ብትገቡ፥ የዚያ ከተማ ሰዎችም ቢቀበሉአችሁ ያቀረቡላችሁን ብሉ።
9
በውስጥዋ የሚገኙትን ድውያንንም ፈውሱ፤ ‘የእግዚአብሔርም መንግሥት ወደ እናንተ ቀርባለች’ በሉአቸው።
10
ነገር ግን ወደ ማናቸውም ከተማ ብትገቡ፥ የዚያች ከተማ ሰዎችም ባይቀበሉአችሁ ወደ አደባባይዋ ወጥታችሁ የእግራችሁን ትቢያ አራግፉ። እንዲህም በሉ፦
11
ከከተማችሁ የተጣበቀብንን ትቢያ እንኳን እናራግፍላችኋለን፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ እንደ ቀረበች ይህን ዕወቁ።
12
በፍርድ ቀን ሰዶም ከዚያች ከተማ ይልቅ እንደምትሻል ይቅርታንም እንደምታገኝ እነግራችኋለሁ።
13
“ኮራዚ ወዮልሽ! ቤተ ሳይዳ ወዮልሽ! በእናንተ የተደረገው ተአምራት በጢሮስና በሲዶና ተደርጎ ቢሆን ቀድሞ ማቅ ለብሰው አመድም ነስንሰው በተቀመጡ ንስሓም በገቡ ነበር።
14
ነገር ግን ጢሮስና ሲዶና ከእናንተ ይልቅ በፍርድ ቀን ይቅርታን ያገኛሉ።
15
አንቺም ቅፍርናሆም እስከ ሰማይ ድረስ ከፍ ከፍ ብትዪ እስከ ሲኦል ትወርጃለሽ።
16
“እናንተን የሚሰማ እኔን ይሰማል፤ እናንተንም እንቢ የሚል እኔን እንቢ ይላል፤ እኔንም እንቢ የሚል የላከኝን እንቢ ይላል፤ እኔንም የሚሰማ የላከኝን ይሰማል።”
17
እነዚያም ሰባው ደስ ብሎአቸው ተመለሱና፥ “አቤቱ፥ አጋንንት ስንኳ በስምህ ተገዙልን” አሉት።
18
እርሱም እንዲህ አላቸው፥ “ሰይጣንን ከሰማይ እንደ መብረቅ ሲወድቅ አየሁት።
19
እነሆ፥ ጊንጦችንና እባቦችን፥ የጠላትንም ኀይል ሁሉ ትረግጡ ዘንድ ሥልጣንን ሰጠኋችሁ፤ የሚጐዳችሁም ነገር የለም።
20
ነገር ግን አጋንንት ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ፤ ግን ስማችሁ በሰማያት ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ።”
21
በዚያች ሰዓትም ጌታችን ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ደስ አለው፤ እንዲህም አለ፥ “የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ፥ ይህን ከዐዋቂዎችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለገለጥኸው አመሰግንሃለሁ፤ አዎን፥ አባት ሆይ፥ ፈቃድህ በፊትህ እንዲሁ ሆኖአልና።
22
ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጠኝ፤ ወልድ ማን እንደ ሆነ ከአብ በቀር የሚያውቅ የለም፤ አብም ማን እንደ ሆነ ከወልድ በቀር የሚያውቅ የለም። ወልድ ግን ለወደደው ይገልጥለታል።”
23
ተመልሶም ደቀ መዛሙርቱን ለብቻቸው አድርጎ እንዲህ አላቸው፥ “እናንተ የምታዩትን የሚያዩ ዐይኖች ብፁዓን ናቸው።
24
ብዙ ነቢያትና ነገሥታት እናንተ የምታዩትን ሊያዩ ተመኙ፤ አላዩምም፤ እናንተ የምትሰሙትንም ሊሰሙ ተመኙ፥ አልሰሙም።”
25
ከዚህ በኋላ አንድ ሕግ ዐዋቂ ሊፈትነው ተነሣና፥ “መምህር ሆይ፥ የዘለዓለም ሕይወትን እወርስ ዘንድ ምን ላድርግ?” አለው።
26
እርሱም፥ “በኦሪት ምን ተጽፎአል? እንዴትስ ታነብባለህ?” አለው።
27
እርሱም መልሶ፥ “እግዚአብሔር አምላክህን በፍጹም ልብህ፥ በፍጹም ሰውነትህ፥ በፍጹም ኀይልህ፥ በፍጹም ዐሳብህ ውደደው፤ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ ይላል” አለው።
28
ጌታችን ኢየሱስም፥ “መልካም መልሰሃል፤ እንዲሁ አድርግ፤ ትድናለህም” አለው።
29
ራሱን ሊያከብር ባልንጀራውንም ሊንቅ ወድዶ፥ “ባልንጀራዬ ማነው?” አለው።
30
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፥ “አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ይወርድ ነበር፤ ሽፍቶችም አገኙት፤ ደበደቡት፥ አቈሰሉት፥ ልብሱንም ገፍፈው፤ በሕይወትና በሞት መካከል ጥለውት ሄዱ።
31
አንድ ካህንም በዚያች መንገድ ሲወርድ ድንገት አገኘው፤ አይቶም አልፎት ሄደ።
32
እንዲሁም አንድ ሌዋዊ በዚያ ቦታ አገኘውና፥ አይቶ እንደ ፊተኛው አልፎት ሄደ።
33
አንድ ሳምራዊ ግን በዚያች መንገድ ሲሄድ አገኘው፤ አይቶም አዘነለት።
34
ወደ እርሱም ቀረበ፤ ቍስሉንም አጋጥሞ አሰረለት፤ በቍስሉ ላይም ወይንና ዘይት ጨመረለት፤ በአህያውም ላይ አስቀምጦ እንዲፈውሰው የእንግዶችን ቤት ወደሚጠብቀው ወሰደው፤ የሚድንበትንም ዐሰበ።
35
በማግሥቱም ሁለት ዲናር አውጥቶ ለእንግዳ ቤት ጠባቂው ሰጠውና፦ ‘በዚህ አስታምልኝ፤ ከዚህ የሚበልጥ ለእርሱ የምታወጣው ቢኖር እኔ በተመለስሁ ጊዜ እከፍልሃለሁ’ አለው።
36
እንግዲህ ሽፍቶች ለደበደቡት ሰው ከእነዚህ ከሦስቱ ባልንጀራ የሚሆነው ማንኛው ይመስልሃል?”
37
እርሱም“ምሕረት ያደረገለት ነዋ” አለው፤ ጌታችን ኢየሱስም፥ “እንኪያስ አንተም ሂድና እንዲሁ አድርግ” አለው።
38
ከዚህም በኋላ ሄደው ወደ አንዲት መንደር ገቡ፤ ማርታ የምትባል አንዲት ሴትም በቤቷ ተቀበለችው።
39
ማርያም የምትባል እኅትም ነበረቻት፤ እርስዋም ከጌታችን ኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጣ ትምህርቱን ትሰማ ነበር።
40
ማርታ ግን ብዙ በማዘጋጀት ትደክም ነበር፤ ቆማም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እኅቴ ትታኝ ብቻዬን ስሠራ አያሳዝንህምን? ርጃት በላት” አለችው።
41
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላት፥ “ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትደክሚያለሽ፥ ትቸገሪያለሽም፤ ታዘጋጂያለሽም።
42
ጥቂት ይበቃል፤ ያም ባይሆን አንድ ይበቃል፤ ማርያምስ የማይቀሙአትን መልካም ዕድል መረጠች።”
← Chapter 9
Chapter 11 →