bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Joshua 14
Joshua 14
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
የእስራኤልም ልጆች በከነዓን ምድር የወረሱት ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ፥ የእስራኤልም ልጆች ነገድ የአባቶቻቸው አለቆች ያወረሱአቸው ርስት ይህ ነው።
2
እግዚአብሔር በሙሴ እጅ እንዳዘዘ ለዘጠኙ ነገድና ለእኩሌታው በየርስታቸው በዕጣ አከፋፈሉአቸው።
3
ለሁለቱ ነገድና ለእኩሌታው ነገድ በዮርዳኖስ ማዶ ሙሴ ርስት ሰጥቶ ነበር፤ ነገር ግን በመካከላቸው ለሌዋውያን ርስት አልሰጣቸውም።
4
የዮሴፍ ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ሁለት ነገዶች ነበሩ፤ ለሌዋውያንም ከሚቀመጡባቸው ከተሞች ለእንስሶቻቸው ከሚሆን ማሰማሪያቸውና ከእንስሶቻቸውም በቀር በምድሩ ውስጥ ድርሻ አልሰጡአቸውም።
5
እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘ እንዲሁ የእስራኤል ልጆች አደረጉ፤ ምድሪቱንም ተካፈሉ።
6
የይሁዳም ልጆች በጌልገላ ወደ ኢያሱ ቀረቡ፤ ቄኔዛዊውም የዮፎኒ ልጅ ካሌብ አለው፥ “ለአምላክ ሰው ለሙሴ ስለ እኔና ስለ አንተ እግዚአብሔር በቃዴስ በርኔ የተናገረውን ቃል ታውቃለህ።
7
የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ምድርን እሰልል ዘንድ ከቃዴስ በርኔ በላከኝ ጊዜ እኔ የአርባ ዓመት ሰው ነበርሁ፤ እኔም በልቡ የነበረውን ቃል መለስሁለት።
8
ከእኔ ጋር የወጡ ወንድሞች ግን የሕዝቡን ልብ አስካዱ፤ እኔ ግን አምላኬን እግዚአብሔርን ፈጽሜ እከተለው ዘንድ ተመለስሁ።
9
ሙሴም በዚያ ቀን፦ ‘አምላኬን እግዚአብሔርን ፈጽመህ ተከትለሃልና እግርህ የረገጠው ምድር ለአንተና ለልጆችህ ለዘለዓለም በርግጥ ርስት ይሆናል’ ብሎ ማለ።
10
አሁንም፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር ለሙሴ ይህን ቃል ከተናገረ በኋላ፥ እስራኤል በምድረ በዳ ሲዞሩ፥ እርሱ እንደ ተናገረኝ እግዚአብሔር እነዚህን አርባ አምስት ዓመታት በሕይወት አኖረኝ፤ አሁንም፥ እነሆ፥ ለእኔ ዛሬ ሰማንያ አምስት ዓመት ሆነኝ።
11
ሙሴም በላከኝ ጊዜ ጽኑዕ እንደ ነበርሁ፥ ዛሬም ገና እንዲሁ ለመዋጋት ለመውጣትም ለመግባትም ጽኑዕ ነኝ።
12
አሁን እንግዲህ በዚያ ቀን እግዚአብሔር የተናገረውን ይህን ተራራማ ሀገር ስጠኝ፤ አንተ በዚያ ቀን ዔናቃውያን፥ ታላላቆችና የተመሸጉ ከተሞችም በዚያ እንዳሉ ሰምተህ ነበር፤ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ቢሆን እግዚአብሔር እንደ ተናገረኝ አጠፋቸዋለሁ።”
13
ኢያሱም የቄኔዝ ልጅ፥ የዮፎኒ ልጅ ካሌብን ባረከው፤ ኬብሮንንም ርስት አድርጎ ሰጠው።
14
ስለዚህም የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ፈጽሞ ስለ ተከተለ ኬብሮን እስከ ዛሬ ለቄኔዛዊው ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ርስት ሆነች።
15
የኬብሮንም ስም አስቀድሞ የአርቦቅ ከተማ ትባል ነበር፤ እርስዋም የዔናቃውያን ዋና ከተማ ነበረች። ምድሪቱም ከውጊያ ዐረፈች።
← Chapter 13
Chapter 15 →