bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Joshua 12
Joshua 12
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
የእስራኤልም ልጆች የመቱአቸው፥ ከአርኖንም ሸለቆ ጀምሮ እስከ አርሞንዔም ተራራ ድረስ በምሥራቅ በኩል ያለውን ዓረባ ሁሉ በዮርዳኖስም ማዶ በፀሐይ መውጫ ያለውን ሀገራቸውን የወረሱአቸው የምድር ነገሥት እነዚህ ናቸው፤
2
በሐሴቦን የተቀመጠው፥ በአርኖንም ሸለቆ አጠገብ ካለችው ከአሮዔር፥ ከሸለቆውም መካከል ጀምሮ የገለዓድን እኩሌታ እስከ ኢያቦቅ ወንዝ እስከ አሞን ልጆች ዳርቻ ድረስ፤
3
በምሥራቅም በኩል ያለውን ዓረባ እስከ ኬኔሬት ባሕር ድረስ፥ በአሴሞት መንገድ አጠገብ እስካለው እስከ ዓረባ ባሕር እስከ ጨው ባሕር ድረስ፥ በደቡብም በኩል ከፋስጋ ተራራ አፋፍ በታች ያለውን ምድር የገዛው የአሞሬዎናውያን ንጉሥ ሴዎን፤
4
ከረዓይት ወገን የቀረ፥ በአስጣሮትና በኤንድራይን የተቀመጠው፥
5
የአርሞንኤምን ተራራ፥ ካሴኪን፥ ባሳንንም ሁሉ እስከ ጌርጌሲና እስከ መከጢ ዳርቻ፥ የገለዓድንም እኩሌታ እስከ ሐሴቦን ንጉሥ እስከ ሴዎን ዳርቻ ድረስ የገዛው የባሳን ንጉሥ ዐግ፤
6
የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴና የእስራኤል ልጆች ገደሉአቸው፤ የእግዚአብሔርም አገልጋይ ሙሴ ርስት አድርጎ ለሮቤል ልጆች፥ ለጋድም ልጆች፥ ለምናሴም ነገድ እኩሌታ ምድሪቱን ሰጣቸው።
7
የእስራኤል ልጆችና ኢያሱ በሊባኖስ ቆላ፥ በበላጋድ ባሕር፥ በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ሴይር በሚደርስ በኬልኪ ተራራ የገደሉአቸው የከነዓን ነገሥት እነዚህ ናቸው። ኢያሱም ያችን ምድር ለእስራኤል ወገኖች ሰጣቸው።
8
በተራራና በሜዳ በዓረባ፥ በአሴዶት በቆላው፥ በናጌብ፥ በኬጤዎንና በአሞሬዎን፥ በከናኔዎንና በፌርዜዎን፥ በኢያቡሴዎንና በኤዌዎን ያለ ርስታቸውን አወረሳቸው።
9
የኢያሪኮ ንጉሥ፥ በቤቴል አጠገብ ያለችው የጋይ ንጉሥ፥
10
የኢየሩሳሌም ንጉሥ፥ የኬብሮን ንጉሥ፥
11
የኢያሪሙት ንጉሥ፥ የለኪስ ንጉሥ፥
12
የኤላም ንጉሥ፥ የጋዜር ንጉሥ፥
13
የዳቤር ንጉሥ፥ የጋሴ ንጉሥ፥
14
የኤርሞት ንጉሥ፥ የዓራድ ንጉሥ፥
15
የልብና ንጉሥ፥ የዓዶላም ንጉሥ፥
16
የመቄዳ ንጉሥ፥
17
የኤጣፋድ ንጉሥ፥
18
የኦፌር ንጉሥ፥
19
የአፌጠቀሰሩት ንጉሥ፥ የአሶር ንጉሥ፥
20
የስሚዖን ንጉሥ፥ የመምሮት ንጉሥ፥
21
የአዚፍ ንጉሥ፥ የቃዴስ ንጉሥ፥
22
የዘቃክ ንጉሥ፥ የማርዶት ንጉሥ፥ በቀርሜሎስ የነበረ የዴቆም ንጉሥ፥
23
በፌናድር ክፍል የምትሆን የኤዶር ንጉሥ፥ በጋልያ ክፍል የምትሆን የሐጌ ንጉሥ፥ የቲርሣ ንጉሥ፥
24
እነዚህ ነገሥት ሁሉ ሃያ ዘጠኝ ናቸው።
← Chapter 11
Chapter 13 →