bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Jeremiah 30
Jeremiah 30
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው። እንዲህም አለው፤
2
“የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የነገርሁህን ቃል ሁሉ በመጽሐፍ ጻፍ።
3
እነሆ! የሕዝቤን የእስራኤልንና የይሁዳን ምርኮ የምመልስበት ዘመን ይመጣልና፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ለአባቶቻቸውም ወደ ሰጠኋት ምድር እመልሳቸዋለሁ፤ እነርሱም ይገዙአታል።”
4
እግዚአብሔር በእስራኤልና በይሁዳ ላይ የተናገረው ቃል ይህ ነው።
5
እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፥ “የሚያስፈራ ድምፅ ትሰማላችሁ፤ ፍርሀት ነው እንጂ ሰላም አይደለም።
6
ጠይቁ፤ ወንድ ይወልድ እንደ ሆነ ተመልከቱ፤ ስለ ምን ሰው ሁሉ እንደ ወላድ እጁን በወገቡ ላይ አድርጎ፥ ፊቱም ሁሉ ወደ ጥቍረት ተለውጦ አየሁ?
7
ወዮ! ያ ቀን ታላቅ ነውና፥ እርሱንም የሚመስል የለምና፤ ያ የያዕቆብ መከራ ዘመን ነው፤ ነገር ግን ከእርሱ ይድናል።
8
በዚያ ቀን እንዲህ ይሆናል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ቀንበርን ከአንገትህ እሰብራለሁ፤ እስራትህንም እበጥሳለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ለሌላ አትገዛም።
9
ለአምላካቸው ለእግዚአብሔርም፥ ለማስነሣላቸው ለንጉሣቸው ለዳዊትም ይገዛሉ።
10
“እነሆ አንተን ከሩቅ፥ ዘርህንም ከምርኮ ሀገር አድናለሁና ባሪያዬ ያዕቆብ ሆይ! አትፍራ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ አንተም እስራኤል ሆይ! አትደንግጥ፤ ያዕቆብም ይመለሳል፤ ያርፍማል፤ ተዘልሎም ይቀመጣል፤ ማንም አያስፈራውም።
11
አድንህ ዘንድ ከአንተ ጋር ነኝና፥ ይላል እግዚአብሔር፤ አንተንም የበተንሁባቸውን አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁ፤ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፤ በመጠን እቀጣሃለሁ፥” ያለ ቅጣትም ከቶ አልተውህም።”
12
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ስብራትህ የማይፈወስ፥ ቍስልህም ክፉ ነው።
13
ትጠገን ዘንድ ክርክርህን የሚፈርድልህ ሰው የለም፤ ቍስልህንም የሚፈውስ መድኀኒት የለህም።
14
ወዳጆችህ ሁሉ ረስተውሃል፤ አይፈልጉህምም፤ በደልህ ታላቅ ስለ ሆነ፥ ኀጢአትህም ስለ በዛ፥ በጠላት ማቍሰልና በጨካኝ ቅጣት አቍስዬሃለሁና።
15
ቍስልህ የማይፈወስ ሆኖአልና ስለ ስብራትህ ለምን ትጮኻለህ? በደልህ ታላቅ ስለ ሆነ፥ ኀጢአትህም ስለ በዛ፥ ይህን አድርጌብሃለሁ።
16
ስለዚህ የሚበሉህ ሁሉ ይበላሉ፤ የሚማርኩህም ሁላቸው ይማረካሉ፤ የዘረፉህም ይዘረፋሉ፤ የሚማርኩህንም ሁሉ ለመማረክ አሳልፌ እሰጣለሁ።
17
እኔ ከክፉ ቍስልሽ እፈውስሻለሁ፤ ጤናሽን እመልስልሻለሁ፤ ቍስልሽንም እፈውሳለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ማንም የማይሻት፥ የተጣለች ጽዮን ብለው ጠርተውሻልና።”
18
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ የያዕቆብን ድንኳን ምርኮ እመልሳለሁ፤ ለማደሪያውም እራራለሁ፤ ከተማዪቱም በጕብታዋ ላይ ትሠራለች፤ አዳራሹም እንደ ዱሮው የሰው መኖሪያ ይሆናል።
19
ከእርሱም ዘንድ የምስጋናና የዘፈን ድምፅ ይወጣል፤ እኔም አበዛቸዋለሁ፤ አያንሱምም።
20
ልጆቻቸውም እንደ ቀድሞው ይሆናሉ፤ ምስክርነታቸውም በፊቴ ጸንቶ ይኖራል፤ የሚያስጨንቁአቸውንም ሁሉ እቀጣለሁ።
21
አለቃቸውም ከእነርሱ ውስጥ ይሾማል፤ ገዢአቸውም ከመካከላቸው ይወጣል፤ እሰበስባቸዋለሁ፤ ወደ እኔም እመልሳቸዋለሁ፤ ወደ እኔ ይመለስ ዘንድ ልብ የሰጠው ማን ነው? ይላል እግዚአብሔር።
22
እናንተም ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ።”
23
እነሆ የእግዚአብሔር ቍጣ ለመቅሠፍት ወጥቶአል፤ የመዓቱንም ጥፋት በኃጥኣን ራስ ላይ አምጥቶአል፤
24
የእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ የልቡን አሳብ ሠርቶ እስኪፈጽም ድረስ አይመለስም፤ በኋለኛውም ዘመን ታውቁታላችሁ።
← Chapter 29
Chapter 31 →