bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Isaiah 6
Isaiah 6
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
ከዚህም በኋላ ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን በረዥምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፤ ምስጋናውም ቤቱን ሞልቶት ነበር።
2
ሱራፌልም በዙሪያው ቆመው ነበር፤ ለእያንዳንዱም ስድስት ክንፍ ነበረው፤ በሁለቱ ክንፎቻቸው ፊታቸውን ይሸፍኑ ነበር፤ በሁለቱም ክንፎቻቸው እግሮቻቸውን ይሸፍኑ ነበር፤ በሁለቱም ክንፎቻቸው ይበርሩ ነበር።
3
አንዱም ለአንዱ፥ “ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች” እያለ ይጮኽ ነበር።
4
የመድረኩም መሠረት ከጩኸታቸው ድምፅ የተነሣ ተናወጠ፤ ቤቱንም ጢስ ሞላበት።
5
እኔም፥ “ከንፈሮች የረከሱብኝ ሰው በመሆኔ፥ ከንፈሮቻቸው በረከሱባቸው ሕዝብ መካከል በመቀመጤ ዐይኖች የሠራዊትን ጌታ ንጉሡን እግዚአብሔርን ስለ አዩ ጠፍቻለሁና ወዮልኝ!” አልሁ።
6
ከሱራፌል አንዱ ወደ እኔ ተላከ፤ በእጁም ከመሠዊያው በጕጠት የወሰደው ፍም ነበረ።
7
አፌንም ዳሰሰበትና፥ “እነሆ፥ ይህ ከንፈሮችህን ነክቶአል፤ በደልህም ከአንተ ተወገደ፤ ኀጢአትህም ተሰረየልህ” አለኝ።
8
የጌታንም ድምፅ፥ “ማንን እልካለሁ? ማንስ ወደዚያ ሕዝብ ይሄድልናል?” ሲል ሰማሁ? እኔም፥ “እነሆኝ፥ ጌታዬ፥ እኔን ላከኝ” አልሁ።
9
እርሱም፥ “ሂድ፤ ይህን ሕዝብ፦ መስማትን ትሰማላችሁ፥ አታስተውሉምም፤ ማየትንም ታያላችሁ፥ አትመለከቱምም” በላቸው አለኝ።
10
እነዚህ ሕዝቦች በዐይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፥ ልባቸውን አደንድነዋልና፥ ጆሮአቸውንም ደፍነዋልና፥ ዐይኖቻቸውንም ጨፍነዋልና።
11
እኔም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ ነው?” አልሁ። እርሱም መልሶ እንዲህ አለኝ፥ “ከተሞች የሚኖርባቸውን አጥተው እስኪፈርሱ ድረስ፥ ቤቶችም ሰው አልቦ እስኪሆኑ፥ ምድርም ፈጽሞ ባድማ ሆና እስክትቀር ድረስ ነው፤”
12
ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ሰዎችን ያርቃል፤ በምድርም የቀሩት ይበዛሉ።
13
በእርስዋም ዘንድ ዐሥረኛ እጅ ቀርቶ እንደ ሆነ እርሱ ደግሞ ይቃጠላል፤ ቅጠሎቻቸውም በረገፉ ጊዜ እንደ ግራርና እንደ ኮምበል ዛፍ ሁነው ይቀራሉ።
← Chapter 5
Chapter 7 →