bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Isaiah 39
Isaiah 39
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
በዚያም ወራት የባቢሎን ንጉሥ የባልዳን ልጅ መሮዳክ ባልዳን ሕዝቅያስ ታምሞ እንደ ተፈወሰ ሰምቶ ነበርና ደብዳቤና እጅ መንሻን፥ መልእክተኞችንም ላከለት።
2
ሕዝቅያስም ስለ እነርሱ እጅግ ደስ አለው፤ ግምጃ ቤቱንም፥ ወርቁንና ብሩን፥ ከርቤውንና ዕጣኑን፥ ዘይቱንም፥ መሣሪያም ያለበትን ቤት ሁሉ፥ ልብሱንና ዕንቍውን ሁሉ፥ በቤተ መዛግብቱም የተገኘውን ሁሉ አሳያቸው፤ በቤቱና በግዛቱ ሁሉ ካለው ሕዝቅያስ ያላሳያቸው የለም።
3
ነቢዩም ኢሳይያስ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ መጥቶ፥ “እነዚህ ሰዎች ምን አሉ? ከወዴትስ መጡ?” አለው። ሕዝቅያስም፥ “ከሩቅ ሀገር ከባቢሎን መጡ” አለው።
4
ኢሳይያስም፥ “በቤትህ ያዩት ምንድን ነው?” አለው፤ ሕዝቅያስም፥ “በቤቴ ያለውን ሁሉ አይተዋል፤ በቤቴ፥ እንዲሁም በቤተ መዛግብቴ ካለው ያላሳየኋቸው የለም” አለው።
5
ኢሳይያስም ሕዝቅያስን፥ “የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ።
6
እነሆ፥ በቤትህ ያለው ሁሉ፥ አባቶችህም እስከ ዛሬ ድረስ ያከማቹት ሁሉ ወደ ባቢሎን የሚፈልስበት ወራት ይመጣል፤ ምንም አያስቀሩልህም፤ ይላል እግዚአብሔር።
7
ከአንተ ከሚወጡት ከምትወልዳቸው ልጆችህ ማርከው ይወስዳሉ፤ በባቢሎንም ንጉሥ ቤት ውስጥ ጃንደረቦችና የቤት አሽከሮች ይሆናሉ” አለው።
8
ሕዝቅያስም ኢሳይያስን፥ “እርሱ የተናገረው የእግዚአብሔር ቃል መልካም ነው፤ ነገር ግን፦ በዘመኔ ሰላምና ጽድቅ ይሁን” አለው።
← Chapter 38
Chapter 40 →