bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Isaiah 35
Isaiah 35
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
የተጠማው ምድረ በዳ ደስ ይለዋል፤ በረሃውም ሐሤት ያደርጋል፤ እንደ ጽጌረዳም ያብባል።
2
የዮርዳኖስም ምድረ በዳ ያብባል፤ ሐሤትንም ያደርጋል፤ የሊባኖስ ክብርና የቀርሜሎስ ክብር ይሰጠዋል፤ ሕዝቤም የጌታን ክብር፥ የአምላክንም ግርማ ያያሉ።
3
ደካሞች እጆችና አንካሶች ጕልበቶች፥ ጽኑ።
4
እናንተ አእምሮ የሌላችሁ፥ ልቡናችሁን አረጋጉ፤ ጽኑ፤ አትፍሩ፤ እነሆ፥ አምላካችን ፍርድን ይመልሳል፤ ይበቀላልም፤ እርሱም መጥቶ ያድነናል።
5
በዚያን ጊዜም የዕውሮች ዐይኖቻቸው ይገለጣሉ፤ የደንቆሮዎችም ጆሮዎች ይሰማሉ።
6
በዚያን ጊዜ አንካሳዎች እንደ ሚዳቋ ይዘልላሉ፤ የዲዳዎችም ምላስ ርቱዕ ይሆናል፤ በምድረ በዳ ውኃ፥ በተጠማ መሬትም ፈሳሽ ይፈልቃልና።
7
ደረቂቱ ምድር ኩሬ፥ የተጠማች ምድርም የውኃ ምንጭ ትሆናለች፤ የዎፎች መኖሪያም ሸንበቆና ደንገል ይሆንበታል።
8
በዚያም ንጹሕ መንገድ ይሆናል፤ እርሱም የተቀደሰ መንገድ ይባላል፤ በዚያም ንጹሓን ያልሆኑ አያልፉበትም፤ ርኩስ መንገድም በዚያ አይኖርም፤ የተበተኑትም በእርሱ ይሄዳሉ፤ አይሳሳቱምም።
9
አንበሳ አይኖርበትም፤ ክፉ አውሬም አይወጣበትም፤ በዚያም አይገኙም፤ የዳኑት ግን በዚያ ይሄዳሉ።
10
በእግዚአብሔር የተሰበሰቡም ይመለሳሉ፤ በደስታም ተመልሰው ወደ ጽዮን ይመጣሉ፤ የዘለዓለም ደስታም በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ ሐሤትንና ደስታንም ያገኛሉ፤ መከራ፥ ኀዘንና ትካዜም ይጠፋሉ።
← Chapter 34
Chapter 36 →