bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Isaiah 18
Isaiah 18
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
በኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ ላለች፥ ክንፍ ያላቸው መርከቦች ላሉባት ምድር ወዮላት!
2
መልእክተኞችን በባሕር ላይ፥ ደብዳቤዎችንም በውኃ ላይ ይልካል። ፈጣኖች መልእክተኞች ወደ ረዥምና ወደ ባዕድ፥ ወደ ክፉም ሕዝብ ይሄዳሉና፤ ተስፋ የቈረጡና የተረገጡ ሕዝብ እነማን ናቸው? ዛሬ ግን የምድር ወንዞች ሁሉ፥ ሰዎች እንደሚኖሩባት ሀገር ይኖራሉ።
3
በየሀገራቸው ይቀመጣሉ፤ ከተራሮች ራሶችም እንደ ዓላማ ይይዙታል፤ እንደ መለከት ድምፅም ይሰማል።
4
እግዚአብሔር፥ “እንደ ቀትር ብርሃን፥ በአጨዳም ወራት እንደ ጠል ደመና በማደሪያዬ ጸጥታ ይሆናል” ብሎኛልና።
5
እርሱ ከመከር በፊት አበባ በረገፈ ጊዜ የወይንም ፍሬ ጨርቋ ሲይዝ የወይኑን ቀጫጭን ዘንግ በማጭድ ይቈርጣል፤ ጫፎቹንም ይመለምላል፤ ያስወግድማል።
6
ለሰማይ ወፎችና ለምድር አውሬዎችም በአንድነት ይቀራሉ፤ የሰማይ ወፎችና የምድር አውሬዎችም ሁሉ ይሰበሰቡባቸዋል።
7
በዚያ ዘመን ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር፥ ከተዋረደና ከደከመ ሕዝብ፥ ከዛሬ እስከ ዘለዓለም ታላቅ ከሆነ ወገን፥ ተስፋ ከሚያደርግና ከሚረገጥ፥ በሀገሩ ወንዝ ዳር ከሚኖር ሕዝብ ዘንድ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ስም በተጠራበት በደብረ ጽዮን እጅ መንሻ ይቀርባል።
← Chapter 17
Chapter 19 →