bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Isaiah 15
Isaiah 15
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
ስለ ሞዓብ የተነገረ ቃል። ሞዓብ በሌሊት ትጠፋለች፤ የሞዓብም ምሽግ በሌሊት ይፈርሳል።
2
ለራሳችሁ እዘኑ፤ ጣዖታችሁና መሠዊያችሁ ያሉባት ዲቦን ትጠፋለችና፤ ወደዚያም ወጥታችሁ በሞዓብ ናባው አልቅሱ፤ ወዮም በሉ፤ ራስ ሁሉ በራ ይሆናል፤ ክንድም ሁሉ ይቈረጣል።
3
በየመንገድዋ ማቅ ታጠቁ፤ በየሰገነቶችዋም አልቅሱ፤ በየአደባባዮችዋም እንባን እጅግ እያፈሰሳችሁ ወዮ በሉ።
4
ሐሴቦንና ኤልያሊ ጮኹ፤ ድምፃቸውም እስከ ያሳ ድረስ ይሰማል፤ ስለዚህ የሞዓብ ወገብ ይታመማል።
5
ሞዓብ ራሷን ይዛ ትጮኻለች፤ ለልቧም ይረዳታል፤ እስከ ሴጎርም ድረስ ብቻዋን ታለቅሳለች። ሞዓብ እንደ ሦስት ዓመት ጥጃ ናትና በሉሒት ዐቀበት ትጮኻለች። በአሮሜዎን መንገድም ይመለሳሉ፤ ይጮኻሉም፥ ጥፋትና መናወጥም ይሆናል።
6
የኔምሬም ውኃ ይነጥፋል፤ ሣሯም ይደርቃል፤ በውስጧም ልምላሜ አይገኝም።
7
ስለዚህ ሞዓብ ይድናልን? ዐረባውያንን ወደ ሸለቆው አመጣቸዋለሁና፤ እነርሱም ይወስዷታል።
8
ጩኸት የሞዓብን ዳርቻ ሁሉ ዞረ፤ ልቅሶዋም ወደ ኤግላይምና ወደ ኢሊም ጕድጓድ ደረሰ።
9
የዲሞንም ውኃ ደም ተሞልታለች፤ በዲሞን ላይ ዐረባውያንን አመጣለሁና፤ የሞዓብንና የአርያልን ዘር፥ ከኤዶምያስም የተረፉትን ወስጄ እንደ አራዊት በምድር ላይ እሰድዳቸዋለሁ።
← Chapter 14
Chapter 16 →