bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Ezekiel 47
Ezekiel 47
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
ወደ መቅደሱም መዝጊያ መለሰኝ፤ እነሆም ውኃ ከቤቱ መድረክ በታች ወደ ምሥራቅ ይወጣ ነበር፤ የቤቱ ፊት ወደ ምሥራቅ ይመለከት ነበርና፤ ውኃውም ከቤቱ ከቀኝ ወገን በታች በመሠዊያው በደቡብ በኩል ይወርድ ነበር።
2
በሰሜኑም በር በኩል አወጣኝ፤ በስተ ውጭ በአለው መንገድ፥ ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከት በስተ ውጭ ወዳለው በር አዞረኝ፤ እነሆም ውኃው በቀኝ በኩል ይፈስስ ነበር።
3
ሰውዮውም የመለኪያ ገመድ በእጁ ይዞ ወደ ምሥራቅ ወጣ፤ አንድ ሺህም ክንድ ለካ፤ በውኃውም ውስጥ አሻገረኝ፤ ውኃውም እስከ ቍርጭምጭሚት ደረሰ።
4
ደግሞ አንድ ሺህ ለካ፤ በውኃውም ውስጥ አሻገረኝ፤ ውኃውም እስከ ጉልበት ደረሰ፤ ደግሞም አንድ ሺህ ለካ፤ በውኃውም ውስጥ አሻገረኝ፤ ውኃውም እስከ ወገብ ደረሰ።
5
ደግሞ አንድ ሺህ ለካ ልሻገረውም የማልችለው ወንዝ ሆነ፤ ውኃውም ጥልቅ ነበረ፤ የሚዋኝበትም ውኃ ነበረ፤ ሰው ሊሻገረው የማይችለው ወንዝ ነበረ።
6
እርሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! አይተሃልን?” አለኝ። አመጣኝም፤ ወደ ወንዙም ዳር መለሰኝ።
7
በተመለስሁም ጊዜ፥ እነሆ በወንዙ ዳር በዚህና በዚያ እጅግ ብዙ ዛፎች ነበሩ።
8
እርሱም እንዲህ አለኝ፥ “ይህ ውኃ ወደ ምሥራቅ ወደ ገሊላ ይወጣል፤ ወደ ዓረባም ይወርዳል፤ ወደ ባሕሩም ይገባል፤ ወደ ባሕሩም ወደ ረከሰው ውኃ በገባ ጊዜ ውኃውን ይፈውሰዋል።
9
ሕያው ነፍስ ያለው ተንቀሳቃሽ ሁሉ ወንዙ በሚገባበት ስፍራ ሁሉ በሕይወት ይኖራል፤ ይህም ውኃ በዚያ ስለ ደረሰ ዓሣዎች እጅግ ይበዛሉ፤ የባሕሩም ውኃ ይፈወሳል፤ ወንዙም በሚመጣበት ያለው ሁሉ በሕይወት ይኖራል።
10
ዓሣ አጥማጆችም ከዓይንጋዲ ጀምሮ እስከ ዓይንኤግላይም ድረስ በዚያ ይቆማሉ። ያም መረብ መዘርጊያ ይሆናል፤ ዓሣዎችም እንደ ታላቁ ባሕር ዓሣዎች በየወገናቸው እጅግ ይበዛሉ።
11
ረግረጉና ዕቋሪው ውኃ ግን ጨው እንደ ሆነ ይኖራል እንጂ አይፈወስም።
12
በወንዙም አጠገብ በዳሩ ላይ በዚህና በዚያ ፍሬው የሚበላ ዛፍ ሁሉ ይበቅላል፤ ቅጠሉም አይረግፍም፤ ፍሬውም አይጐድልም፤ ውኃውም ከመቅደስ ይወጣልና በየወሩ ሁሉ የፍሬ በኵር ያገኛል፤ ፍሬውም ለመብል፥ ቅጠሉም ለመድኀኒት ይሆናል።”
13
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ርስት አድርጋችሁ ለዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ምድሪቱን የምትከፍሉበት ድንበር ይህ ነው። ለዮሴፍ ሁለት ዕጣ ይሆናል።
14
ለአባቶቻችሁ እሰጣቸው ዘንድ እጄን አንሥቼ ነበርና እናንተ እኩል አድርጋችሁ ተካፈሉት፤ ይህችም ምድር ርስት ትሆናችኋለች።
15
“የምድሪቱም ድንበር ይህ ነው። በሰሜኑ ወገን ከታላቁ ባሕር ጀምሮ በሔትሎን መንገድ ወደ ጽዳድ መግቢያ፤
16
ሐማት፥ ቤሮታ፥ በደማስቆ ድንበርና በሐማት ድንበር መካከል ያለው ሲብራይም፥ በሐውራን ድንበር አጠገብ ያለው ሐጸርሃቲኮን።
17
ድንበሩ ከባሕሩ በደማስቆ ድንበር ላይ ያለው ሐጽርዔናን ይሆናል፥ በሰሜን በኩል የሐማት ድንበር አለ። የሰሜኑ ድንበር ይህ ነው።
18
የምሥራቁም ድንበር በሐውራን በደማስቆና በገለዓድ በእስራኤልም ምድር መካከል ዮርዳኖስ ይሆናል። ከሰሜኑ ድንበር ጀምሮ እስከ ምሥራቁ ባሕር እስከ ታማር ድረስ የምሥራቁ ድንበር ይህ ነው።
19
የደቡቡም ድንበር ከታማር ጀምሮ እስከ ሜሪባ ቃዴስ ውኃ እስከ ግብፅ ወንዝ እስከ ታላቁ ባሕር ይሆናል። የደቡቡም ድንበር ይህ ነው።
20
የምዕራቡም ድንበር ከደቡቡ ድንበር ጀምሮ እስከ ሐማት መግቢያ አንጻር ድረስ ታላቁ ባሕር ይሆናል። የምዕራቡ ድንበር ይህ ነው።
21
“ይህችን ምድር እናንተ ዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል ትከፋፈላላችሁ።
22
ለእናንተና በእናንተ መካከል ለሚቀመጡ፥ በእናንተም መካከል ልጆችን ለሚወልዱ መጻተኞች ርስት አድርጋችሁ በዕጣ ትካፈሉአታላችሁ፤ እነርሱም በእስራኤል ልጆች መካከል እንደ አሉ የሀገር ልጆች ይሆኑላችኋል፤ በእስራኤልም ነገዶች መካከል ከእናንተ ጋር ርስትን ይወርሳሉ።
23
መጻተኛውም በማናቸውም ነገድ መካከል ቢቀመጥ በዚያ ርስትን ትሰጡታላችሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
← Chapter 46
Chapter 48 →