bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Ezekiel 32
Ezekiel 32
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
እንዲህም ሆነ፤ በዐሥራ ሁለተኛው ዓመት በዐሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦
2
“የሰው ልጅ ሆይ! ስለ ግብፅ ንጉሥ ስለ ፈርዖን ሙሾ አሙሽ፤ እንዲህም በለው፦ የአሕዛብን አንበሳ መስለህ ነበር፤ ነገር ግን እንደ ባሕር ዘንዶ ሆነሃል፤ ወንዞችህንም ወግተሃል፤ ውኃውንም በእግርህ አደፍርሰሃል፥ ወንዞችህንም በተረከዝህ ረግጠሃል።
3
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በብዙ አሕዛብ ጉባኤ መረቤን እዘረጋብሃለሁ፤ በመረቤም አወጣሃለሁ።
4
በሰፊ ምድረ በዳም እጥልሃለሁ፤ የሰማይንም ወፎች ሁሉ አሳርፍብሃለሁ፤ የምድርንም አራዊት ሁሉ ከአንተ አጠግባቸዋለሁ።
5
ሥጋህን በተራሮች ላይ አደርጋለሁ፤ በደምህም አረካቸዋለሁ።
6
የምቷኝባትንም ምድር እስከ ተረራሮች ድረስ በደምህ አጠጣለሁ፤ መስኖዎችም ከአንተ ይሞላሉ።
7
በጠፋህም ጊዜ ሰማዮችን እሸፍናለሁ፤ ከዋክብትንም አጨልማለሁ፤ ፀሐዩንም በደመና እሸፍናለሁ፤ ጨረቃም ብርሃኑን አይሰጥም።
8
የሰማይን ብርሃኖች ሁሉ በላይህ አጨልማለሁ፤ በምድርህም ላይ ጨለማን አደርጋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
9
በማታውቃቸውም ሀገሮች በአሉ በአሕዛብ ዘንድ ድል መሆንህን በአሰማሁ ጊዜ የብዙ ሕዝብን ልብ አስጨንቃለሁ።
10
ብዙ አሕዛብን አስደንቅብሃለሁ፤ ሰይፌም በፊታቸው በተወረወረች ጊዜ ንጉሦቻቸው እጅግ አድርገው ይፈራሉ፤ በወደቅህባትም ቀን እያንዳንዱ ስለ ነፍሱ በየጊዜው ይንቀጠቀጣል።”
11
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፥ “የባቢሎን ንጉሥ ሰይፍ ይመጣብሃል።
12
በኀያላን ሰይፍ ኀይልህን እጥላለሁ፤ ሁሉ የአሕዛብ ጨካኞች ናቸው፤ የግብፅንም ትዕቢት ያጠፋሉ፤ ኀይልዋም ሁሉ ይደመሰሳል።
13
በብዙም ውኃ አጠገብ ያሉትን እንስሶች ሁሉ አጠፋለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲያ የሰው እግር አያደፈርሳትም፤ የእንስሳም ኮቴ አይረግጣትም።
14
በዚያን ጊዜ ውኆቻቸውን አጠራለሁ፤ ወንዞቻቸውም እንደ ዘይት ይፈስሳሉ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
15
የግብፅንም ምድር ባድማና ውድማ በአደረግሁ ጊዜ፥ ምድርም በመላዋ በጠፋች ጊዜ፥ የሚኖሩባትንም ሁሉ በቀሠፍሁ ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
16
ይኸውም ሙሾ ነው፤ ሙሾን ያሞሹለታል፤ የአሕዛብ ሴቶች ልጆች ያሞሹለታል፤ ስለ ግብፅና ስለ ኀይልዋ ሁሉ ያሞሹለታል፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
17
እንዲህም ሆነ፤ በዐሥራ ሁለተኛው ዓመት በመጀመሪያው ወር ከወሩም በዐሥራ አምስተኛው ቀን የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦
18
“የሰው ልጅ ሆይ! ስለ ግብፅ ኀይል ዋይ በል፤ እርስዋንና የብርቱዎቹን አሕዛብ ሴቶች ልጆች ወደ ጕድጓድ ከሚወርዱ ጋር ወደ ታችኛው ምድር ጣላቸው።
19
በውበት የምትበልጪው ማን ነው? ውረጂ ካልተገረዙትም ጋር ተኚ።
20
በሰይፍ በተገደሉት መካከል ከእርሱ ጋር በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ኀይሉም ሁሉ ይጠፋል፤ እርስዋንና ብዛቷን ሁሉ ጐትቱ።
21
የኀያላን አለቆች በሲኦል ውስጥ ሆነው ከረዳቶቹ ጋር ይናገሩታል፤ በሰይፍም የተገደሉት ያልተገረዙ ወርደው ተኝተዋል።
22
“አሦርና ሠራዊቱ ሁሉ በዚያ ተገደሉ፤ ሁሉም ድል ተነሡ፤ ወደ ጥልቅ ዐዘቅትም ጣሉአቸው ሠራዊቱም በመቃብር ዙሪያ ናቸው፤ ሁሉም በሰይፍ ወድቀው ተገደሉ።
23
መቃብራቸው በጕድጓዱ በውስጠኛው ክፍል ነው፤ ጉባኤዋም በመቃብርዋ ዙሪያ ነው፤ በሕያዋን ምድር ያስፈሩ ሁሉ በሰይፍ ወድቀው ተገድለዋል።
24
“ኤላምም በዚያ አለች፤ ኀይልዋም ሁሉ በመቃብርዋ ዙሪያ ነው፤ በሕያዋን ምድር ያስፈሩ ሁሉ በሰይፍ ወድቀው ተገድለዋል፤ ሳይገረዙም ወደ ታችኛው ምድር ወርደዋል፤ ወደ ጕድጓድም ከሚወርዱ ጋር ቅጣታቸውን አግኝተዋል።
25
በተገደሉት መካከል ከብዛቷ ሁሉ ጋር መኝታን አድርገውላታል፤ መቃብርዋ በዙሪያዋ ነው፤ ሁሉም ያልተገረዙና በሰይፍ የተገደሉ ናቸው፤ በሕያዋንም ምድር ያስፈሩ ነበር፤ ወደ ጕድጓድም ከሚወርዱ ጋር እፍረታቸውን ተሸክመዋል፤ በተገደሉትም መካከል ተሰጥተዋል።
26
“ሞሳሕና ቶቤል፥ ሠራዊታቸውም ሁሉ በዚያ አሉ፤ መቃብራቸውም በዙሪያቸው ነው፤ ሁሉም ሳይገረዙ በሰይፍ ተገድለዋል፤ በሕያዋን ምድር ያስፈሩ ነበርና።
27
በሕያዋንም ምድር ኀያላኑን ያስፈሩ ነበርና፤ መሣሪያቸውን ይዘው ወደ ሲኦል ከወረዱ፥ ሰይፋቸውንም ከራሳቸው በታች ከአደረጉ፥ ኀጢአታቸውም በአጥንታቸው ላይ ከሆነ ጋር ከወደቁ ካልተገረዙ ኀያላን ጋር ይተኛሉ።
28
አንተም ደግሞ ባልተገረዙት መካከል ትሰበራለህ፤ በሰይፍም ከተገደሉት ጋር ትተኛለህ።
29
“ኤዶምያስና ነገሥታቷ፥ አለቆችዋም ሁሉ በዚያ አሉ፤ በሰይፍ ከተገደሉት ጋር
30
ከአልተገረዙና ወደ ጕድጓድ ከሚወርዱ ጋር ተኝተዋል፤ የሰሜን አለቆች ሁሉ፥ ሲዶናውያንም ሁሉ ከተገደሉት ጋር ወርደው በዚያ አሉ፤ በኀይላቸውም ያስፈሩ በነበረው ፍርሀት አፍረዋል፤ በሰይፍም ከተገደሉት ጋር ያልተገረዙት ተኝተዋል፤ ወደ ጕድጓድም ከሚወርዱት ጋር ቅጣታቸውን ተሸክመዋል።
31
“በሰይፍ የተገደሉ ፈርዖንና ሠራዊቱ ሁሉ ያዩአቸዋል፤ ፈርዖንም ስለ ኀይላቸው ሁሉ ይጽናናል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
32
መፈራቴን በሕያዋን ምድር አድርጌአለሁ፤ ፈርዖንና ሠራዊቱ ሁሉ በሰይፍ በተገደሉት፥ ባልተገረዙት መካከል ይተኛሉ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
← Chapter 31
Chapter 33 →