bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Ezekiel 15
Ezekiel 15
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦
2
“የሰው ልጅ ሆይ! የወይን ግንድ ከዱር ዛፎች ሁሉና ከዱር ዛፎች ቅርንጫፎች ሁሉ ይልቅ ብልጫው ምንድን ነው?
3
በውኑ ሥራ የሚሠራበትን እንጨት ከእርሱ ይወስዳሉን? ወይስ ሰዎች ዕቃ የሚንጠለጠልበትን ኩላብ ከእርሱ ይወስዳሉን?
4
እነሆ ለመቃጠል በእሳት ላይ ተጥሎአል፤ እሳቱም ሁለቱን ጫፎቹን በልቶአል፤ መካከሉም ተቃጥሎአል፤ በውኑ ለሥራ ይጠቅማልን?
5
ከውፍረቱም የተነሣ ለሥራ አይሆንም፤ ለምትበላና ለምታጠፋ እሳት ይሆናል እንጂ ከዚያ በኋላ በውኑ ለሥራ ይሆናልን?
6
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዱር ዛፎች መካከል ያለውን የወይን ግንድ እሳት ይበላው ዘንድ እንደ ሰጠሁት፥ እንዲሁ በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን አሳልፌ እሰጣለሁ።
7
ፊቴንም በእነርሱ ላይ አጸናለሁ፤ ከእሳትም አይወጡም፤ እሳትም ይበላቸዋል፤ ፊቴንም በእነርሱ ላይ በአጸናሁ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
8
ዐመፅን አድርገዋልና ምድሪቱን ባድማ አደርጋለሁ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
← Chapter 14
Chapter 16 →