bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
Ecclesiastes 11
Ecclesiastes 11
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
እንጀራህን በውኃ ፊት ላይ ጣለው፥ ከብዙ ቀን በኋላ ታገኝኘዋለህና።
2
ለሰባት፥ ደግሞም ለስምንትዕድል ፈንታን ስጥ፥ በምድር ላይ የሚሆነውን ክፉ ነገር ምን እንደ ሆነ አታውቅምና።
3
ደመናት ዝናም በሞሉ ጊዜ በምድር ላይ ያፈስሱታል፤ ዛፍም ወደ ደቡብ ወይም ወደ ሰሜን ቢወድቅ፥ ዛፉ በወደቀበት ስፍራ በዚያ ይኖራል።
4
ነፋስን የሚጠባበቅ አይዘራም፥ ደመናትንም የሚመለከት አያጭድም።
5
የነፋስ መንገድ እንዴት እንደ ሆነች፥ አጥንትም በእርጉዝ ሆድ እንዴት እንድትዋደድ እንደማታውቅ፥ እንዲሁም ሁሉን የሚሠራውን የእግዚአብሔርን ሥራ አታውቅም።
6
ይህ ወይም ያ ማናቸው እንዲበቅል ወይም ሁለቱ መልካም እንደ ሆኑ አታውቅምና በማለዳ ዘርህን ዝራ፥ በማታም እጅህን አትተው።
7
ብርሃን ጣፋጭ ነው፥ ፀሓይንም ማየት ለዐይን መልካም ነው።
8
ሰው ብዙ ዘመን በሕይወት ቢኖር፥ በሁሉም ደስ ቢለው፤ የጨለማውን ዘመን ያስብ፥ ብዙ ቀን ይሆናልና። የሚመጣውም ነገር ሁሉ ከንቱ ነው።
9
አንተ ጐበዝ፥ በጕብዝናህ ደስ ይበልህ፥ በጕብዝናህም ወራት ልብህን ደስ ይበለው፥ በልብህም መንገድ፥ ዐይኖችህም በሚያዩት ሂድ፤ ዳሩ ግን ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንዲያመጣህ ዕወቅ።
10
ሕፃንነትና ጕብዝና፥ አለማወቅም ከንቱ ናቸውና ከልብህ ቍጣን አርቅ፥ ከሰውነትህም ክፉ ነገርን አስወግድ።
← Chapter 10
Chapter 12 →