bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
2 Samuel 9
2 Samuel 9
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
ዳዊትም፥ “ስለ ዮናታን ቸርነት አደርግለት ዘንድ ከሳኦል ቤት የቀረ አንድ ሰው አለን?” አለ።
2
ከሳኦልም ቤት አንድ ብላቴና ነበረ፤ ስሙም ሲባ ነበረ፤ ወደ ዳዊትም ጠሩት፤ ንጉሡም፥ “አንተ ሲባ ነህን?” አለው። እርሱም፥ “እኔ አገልጋይህ ነኝ” አለ።
3
ንጉሡም፥ “የእግዚአብሔርን ቸርነት አደርግለት ዘንድ ከሳኦል ቤት የቀረ ሰው አለን?” አለ። ሲባም ንጉሡን፥ “እግሮቹ ሽባ የሆኑ አንድ የዮናታን ልጅ አለ” አለው።
4
ንጉሡም፥ “ወዴት ነው?” አለው፤ ሲባም ለንጉሡ፥ “እነሆ እርሱ በሎዶባር በአብያል ልጅ በማኪር ቤት አለ” አለው።
5
ንጉሡም ዳዊት ልኮ ከሎዶባር ከአብያል ልጅ ከማኪር ቤት አስመጣው።
6
የሳኦልም ልጅ የዮናታን ልጅ ሜምፌቡስቴ ወደ ዳዊት መጣ፤ በግንባሩም ወድቆ ሰገደለት፤ ንጉሥ ዳዊትም፥ “ሜምፌቡስቴ ሆይ፥” አለ፤ እርሱም፥ “እነሆኝ አገልጋይህ” አለ።
7
ዳዊትም፥ “ስለ አባትህ ስለ ዮናታን ቸርነት ፈጽሜ አደርግልሃለሁና አትፍራ፤ የአባትህን አባት የሳኦልን መሬት ሁሉ እመልስልሃለሁ፤ አንተም ሁል ጊዜ ከገበታዬ እንጀራን ትበላለህ” አለው።
8
እርሱም፥ “የሞተ ውሻ ወደምመስል ወደ እኔ ትመለከት ዘንድ እኔ አገልጋይህ ምንድን ነኝ?” ብሎ ሰገደ።
9
ንጉሡም የሳኦልን አገልጋይ ሲባን ጠርቶ፥ “ለሳኦልና ለቤቱ ሁሉ የነበረውን ሁሉ ለጌታህ ልጅ ሰጥቻለሁ።
10
አንተና ልጆችህ፥ ሎሌዎችህም ምድሩን እረሱለት፤ ለጌታህም ልጅ እንጀራ ይሆነው ዘንድ ፍሬውን አግቡ፤ እናንተም ትመግቡታላችሁ፤ የጌታህ ልጅ ሜምፌቡስቴ ግን ሁልጊዜ ከገበታዬ ይበላል” አለው። ለሲባም ዐሥራ አምስት ልጆችና ሃያ አገልጋዮች ነበሩት።
11
ሲባም ንጉሡን፥ “ጌታዬ ንጉሡ አገልጋዩን እንዳዘዘ እንዲሁ አገልጋይህ ያደርጋል” አለው። ሜምፌቡስቴም ከንጉሡ ልጆች እንደ አንዱ ከዳዊት ገበታ ይበላ ነበር።
12
ለሜምፌቡስቴም ሚካ የተባለ ታናሽ ልጅ ነበረው፤ በሲባም ቤት ያሉ ሁሉ ለሜምፌቡስቴ ያገለግሉ ነበር።
13
ሜምፌቡስቴም ከንጉሥ ገበታ ሁልጊዜ እየበላ በኢየሩሳሌም ኖረ፤ ሁለት እግሮቹም ሽባ ነበሩ።
← Chapter 8
Chapter 10 →