bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
2 Kings 20
2 Kings 20
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
በዚያም ወራት ሕዝቅያስ ታመመ፤ ለሞትም ደረሰ። ነቢዩም የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ወደ እርሱ መጥቶ፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ትሞታለህ እንጂ በሕይወት አትኖርምና ቤትህን አስተካክል” አለው።
2
ሕዝቅያስም ፊቱን ወደ ግድግዳው መልሶ እንዲህ ሲል ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፦
3
“አቤቱ፥ በፊትህ በእውነትና በፍጹም ልብ እንደ ሄድሁ፥ መልካም ነገርም እንዳደረግሁ አስብ።” ሕዝቅያስም እጅግ አለቀሰ።
4
ኢሳይያስም ወደ መካከለኛው አደባባይ ሲደርስ እግዚአብሔር ተናገረው፤ እንዲህም አለው፦
5
“ተመልሰህ የሕዝቤን ንጉሥ ሕዝቅያስን እንዲህ በለው፦ የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጸሎትህን ሰምቻለሁ፥ እንባህንም አይቻለሁ፤ እነሆ፥ እኔ እፈውስሃለሁ፤ እስከ ሦስት ቀንም ድረስ ወደ እግዚአብሔር ቤት ትወጣለህ።
6
በዕድሜህም ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ፤ አንተንና ይህችን ከተማ ከአሦር ንጉሥ እጅ እታደጋለሁ፤ ስለ እኔ፥ ስለ ባሪያዬም ስለ ዳዊት ይህችን ከተማ አጋርዳታለሁ።”
7
ኢሳይያስም አለው፥ “የበለስ ጥፍጥፍ አምጥተህ በእባጭህ ላይ አድርግ ትፈወሳለህም።”
8
ሕዝቅያስም ኢሳይያስን፥ “እግዚአብሔር እንዲፈውሰኝ፥ እኔስ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንድወጣ ምልክቱ ምንድን ነው?” አለው።
9
ኢሳይያስም፥ “እግዚአብሔር የተናገረውን ነገር እንዲፈጽመው ከእግዚአብሔር ዘንድ ምልክቱ ይህ ይሆንልሃል፤ ጥላው ዐሥር ደረጃ ወደ ፊት ይሂድን? ወይስ ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላው ይመለስ?” አለ።
10
ሕዝቅያስም ኢሳይያስን፥ “ጥላው ዐሥር ደረጃ ቢጨምር ቀላል ነገር ነው፤ እንዲህ አይሁን፤ ነገር ግን ጥላው ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ ይመለሰ” አለው።
11
ነቢዩም ኢሳይያስ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፤ ጥላውም ዐሥር ደረጃ ወደ ኋላ ተመለሰ።
12
በዚያም ወራት የባቢሎን ንጉሥ መሮዳህ ሕዝቅያስ እንደ ታመመ ሰምቶ ነበርና የበልዳንን ልጅ በልዳንን ከመጻሕፍትና እጅ መንሻ ጋር ወደ ሕዝቅያስ ላከ።
13
ሕዝቅያስም በእነርሱ ደስ አለው፤ ግምጃ ቤቱንም ሁሉ፥ ብሩንና ወርቁንም፥ ሽቱውንና የከበረውንም ዘይት፥ መሣሪያም ያለበትን ቤት በቤተ መዛግብቱም የተገኘውን ሁሉ አሳያቸው፤ በቤቱና በግዛቱ ሁሉ ካለው ሕዝቅያስ ያላሳያቸው የለም።
14
ነቢዩ ኢሳይያስም ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ መጥቶ፥ “እነዚህ ሰዎች ምን አሉ? ከወዴትስ ወደ አንተ መጡ?” አለው። ሕዝቅያስም፥ “ከሩቅ ሀገር ከባቢሎን ወደ እኔ መጡ” አለው።
15
እርሱም፥ “ምን አዩ?” አለው ሕዝቅያስም፥ “በቤቴ ያለውን ሁሉ አይተዋል፤ በቤተ መዛግብቴም ካለው ያላሳየኋቸው የለም” አለው።
16
ኢሳይያስም ሕዝቅያስን አለው፥ “የእግዚአብሔርን ቃል ስማ።
17
እነሆ፥ በቤትህ ያለው ሁሉ፥ አባቶችህም እስከ ዛሬ ያከማቹት ሁሉ ወደ ባቢሎን የሚፈልስበት ወራት ይመጣል፤ ምንም አይቀርም፥ ይላል እግዚአብሔር።
18
ከአንተም ከሚወጡት ከምትወልዳቸው ልጆችህ ማርከው ይወስዳሉ፤ በባቢሎንም ንጉሥ ቤት ውስጥ ጃንደረቦች ይሆናሉ።”
19
ሕዝቅያስም ኢሳይያስን፥ “እግዚአብሔር የተናገረው ቃል መልካም ነው። ደግሞም በዘመኔ ሰላም ይሁን” አለው።
20
የቀረውም የሕዝቅያስ ነገር፥ ኀይሉም ሁሉ፥ ኵሬውንና መስኖውን እንደ ሠራ፥ ውኃውንም ወደ ከተማዪቱ እንዳመጣ፥ እነሆ፥ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?
21
ሕዝቅያስም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊት ከተማም ቀበሩት። ልጁ ምናሴም በእርሱ ፋንታ ነገሠ።
← Chapter 19
Chapter 21 →