2 Chronicles 35

Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

19ይህም ፋሲካ ኢዮ​ስ​ያስ በነ​ገሠ በዐ​ሥራ ስም​ን​ተ​ኛው ዓመት ተደ​ረገ። ‘ሀ’ ንጉሡ ኢዮ​ስ​ያስ ካህኑ ኬል​ቅ​ያስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ባገ​ኘው መጽ​ሐፍ የተ​ጻ​ፉ​ትን ቃላት ሁሉ ለመ​ጠ​በቅ አስ​ማ​ተ​ኞ​ች​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ችን፥ ሟር​ተ​ኞ​ች​ንና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ምድ​ርና በይ​ሁዳ የሚ​ገ​ኙ​ትን ምስ​ሎ​ችና ቃሪ​ያ​ሲም የተ​ባሉ ጣዖ​ታ​ትን በእ​ሳት አቃ​ጠለ። ‘ለ’ እንደ ሙሴ ሕግ ሁሉ በፍ​ጹም ልቡ፥ በፍ​ጹም ነፍሱ፥ በፍ​ጹም ኀይሉ ከእ​ርሱ በፊት ከነ​በ​ሩት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ለሰ የሚ​መ​ስ​ለው ሰው አል​ነ​በ​ረም። ከእ​ር​ሱም በኋላ የሚ​መ​ስ​ለው አል​ተ​ነ​ሣም። ‘ሐ’ ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ንጉሥ ምናሴ በይ​ሁዳ ላይ በአ​ደ​ረ​ገ​ውና በአ​ነ​ሣ​ሣው ጥፋት ሁሉ ከአ​ስ​ከ​ተ​ለው ታላቅ ቍጣ አል​ተ​መ​ለ​ሰም። ‘መ’ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “እስ​ራ​ኤ​ልን እን​ዳ​ራ​ቅሁ ይሁ​ዳን ከፊቴ አር​ቃ​ለሁ። የመ​ረ​ጥ​ኋ​ት​ንም ከተማ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንና ስሜ በዚያ ይጠ​ራ​በ​ታል ያል​ሁ​ትን ቤት እጥ​ላ​ለሁ።”
← Chapter 34Chapter 36 →