bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
2 Chronicles 27
2 Chronicles 27
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
ኢዮአታምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሃያ አምስት ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ ስድስት ዓመት ነገሠ፤ እናቱም የሳዶቅ ልጅ ኢየሩሳ ትባል ነበር።
2
አባቱም ዖዝያን እንዳደረገ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገር አደረገ፤ ነገር ግን ወደ እግዚአብሔር መቅደስ አልገባም፤ ሕዝቡም ገና ይበድል ነበር።
3
የእግዚአብሔርን ቤት የላይኛውን በር ሠራ፤ በዖፌልም ቅጥር ላይ ብዙ ሠራ።
4
በተራራማውም በይሁዳ ሀገር ላይ ከተሞችን ሠራ፤ በዱር ስፍራዎችም አምባዎችንና ግንቦችን ሠራ።
5
ከአሞንም ልጆች ንጉሥ ጋር ተዋጋ፤ አሸነፋቸውም። በዚያም ዓመት የአሞን ልጆች መቶ መክሊት ብር፥ ዐሥር ሺህም የቆሮስ መስፈሪያ ስንዴ፥ ዐሥር ሺህም የቆሮስ መስፈሪያ ገብስ ግብር ሰጡት። እንዲሁም ደግሞ የአሞን ልጆችና ንጉሣቸው በመጀመሪያው፥ በሁለተኛውና በሦስተኛው ዓመት ሰጡት።
6
ኢዮአታምም በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት መንገዱን አቅንቶአልና በረታ።
7
የቀሩትም የኢዮአታም ነገሮች፥ ሰልፉም ሁሉ፥ ሥራውም፥ እነሆ፥ በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፎአል።
8
መንገሥም በጀመረ ጊዜ የሃያ አምስት ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ ስድስት ዓመት ነገሠ።
9
ኢዮአታምም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ ቀበሩት፤ ልጁም አካዝ በእርሱ ፋንታ ነገሠ።
← Chapter 26
Chapter 28 →