bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
1 Corinthians 8
1 Corinthians 8
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
ለጣዖታት ስለሚሠዉ መሥዋዕቶች ሁላችንም ዕውቀት እንዳለን እናውቃለን፤ ዕውቀት ያስታብያል፤ ፍቅር ግን ያንጻል።
2
ዐወቅሁ የሚል ቢኖር፥ ሊያውቅ የሚገባውን ገና አላወቀም።
3
እግዚአብሔርን የሚወድ ሰው ግን እርሱ በእርሱ ዘንድ በእውነት የታወቀ ነው።
4
ለጣዖታት የተሠዋውን ስለመብላት ግን ጣዖት ሁሉ በዓለም ከንቱ እንደሆነ፥ ከአንድ እግዚአብሔርም በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ እናውቃለን።
5
አማልክት የሚሉአቸው ነገሮች አሉና፤ በሰማይም ቢሆን፥ በምድርም ቢሆን፥ ብዙ አማልክትና ብዙ ጌቶች ቢኖሩ፥
6
ለእኛስ ሁሉ ከእርሱ የሆነ፥ እኛም ለእርሱ የሆን አንድ እግዚአብሔር አብ አለን፤ ሁሉ በእርሱ የሆነ፥ እኛም በእርሱ የሆን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም አለን።
7
ነገር ግን ሁሉ የሚያውቀው አይደለም፤ እስከ ዛሬ በጣዖታት ልማድ፥ ለጣዖት የተሠዋውን የሚበሉ አሉ፤ ኅሊናቸውም ደካማ ስለሆነ ይረክሳል።
8
መብል ግን ወደ እግዚአብሔር አያደርሰንም፤ ብንበላም አይረባንም፤ ባንበላም አይጎዳንም።
9
ነገር ግን እናንተን በማየት ሌላው እንዳይሰናከል ተጠንቀቁ።
10
አንተ አማኙ በጣዖት ቤት በማዕድ ተቀምጠህ ያየህ ቢኖር ያ ልቡ ደካማ የሆነ ሰው ወዲያው ለጣዖት የተሠዋውን ደፍሮ ይበላል።
11
ክርስቶስ ስለ እርሱ የሞተለት ያ ደካማ ወንድም አንተን በማየት ይጎዳል።
12
በባልንጀሮቻችሁ ላይ እንዲህ የምትበድሉ ከሆነ ደካማ ሕሊናቸውንም የምታቈስሉ ከሆነ ክርስቶስን ትበድላላችሁ።
13
ነገር ግን በመብል ምክንያት ወንድሜ የሚሰናከል ከሆነ ወንድሜን እንዳላሰናክል ለዘለዓለም ሥጋን አልበላም።
← Chapter 7
Chapter 9 →