bible
ra
🌐 Language
English
Español
Français
Deutsch
Português
Italiano
Nederlands
Русский
中文
日本語
한국어
العربية
Türkçe
Tiếng Việt
ไทย
Indonesia
All Languages
Home
/
Amharic
/
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
/
1 Chronicles 20
1 Chronicles 20
Amharic 2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
1
እንዲህም ሆነ፤ በዓመት መጨረሻ ነገሥታት ወደ ሰልፍ በሚወጡበት ጊዜ ኢዮአብ የሠራዊቱን ኀይል አወጣ፤ የአሞንንም ልጆች ሀገር አጠፋ፤ መጥቶም አራቦትን ከበበ። ዳዊትም በኢየሩሳሌም ተቀምጦ ነበር። ኢዮአብም አራቦትን መትቶ አፈረሳት።
2
ዳዊትም የንጉሣቸውን የሞልኮልን ዘውድ ከራሱ ላይ ወሰደ፤ ክብደቱም አንድ መክሊት ወርቅ ያህል ሆኖ ተገኘ፤ ክቡር ዕንቍም ነበረበት፤ በዳዊትም ራስ ላይ አስቀመጡት፤ ከከተማዪቱም እጅግ ብዙ ምርኮ ወሰደ።
3
በውስጥዋም የነበሩትን ሕዝብ አውጥተው በመጋዝ ተረተሩአቸው፤ በመጥረቢያም ቈራረጡአቸው። ዳዊትም በአሞን ልጆች ከተሞች ሁሉ እንዲሁ አደረገ። ዳዊትም ሕዝቡም ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።
4
ከዚህም በኋላ በጋዜር ላይ ከፍልስጥኤማውያን ጋር ጦርነት እንደ ገና ሆነ፤ ያንጊዜም ኡሳታዊው ሴቦቃይ ከኀያላን ወገን የነበረውን ሲፋይን ገድሎ ጣለው።
5
ደግሞም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ሰልፍ ነበረ፤ የያዔርም ልጅ ኤልያናን የጌት ሰው የጎልያድን ወንድም ለሕሜን ገደለ። የጦሩ የቦም እንደ ሸማኔ መጠቅለያ ሆኖ ተገኘ።
6
ደግሞ በጌት ላይ ሰልፍ ሆነ ፤ በዚያም በእጁና በእግሩ ስድስት ስድስት ጣቶች በጠቅላላው ሃያ አራት ጣቶች ያሉት አንድ ረዥም ሰው ነበረ፤ እርሱም ደግሞ ከኀያላን የተወለደ ነበረ።
7
እስራኤልንም በተገዳደረ ጊዜ የዳዊት ወንድም የሳምዓ ልጅ ዮናታን ገደለው።
8
እነዚህም በጌት ውስጥ ከኀያላን የተወለዱ ነበሩ፤ እነርሱም አራት ኀያላን ነበሩ፤ በዳዊትም እጅ በአገልጋዮቹም እጅ ወደቁ።
← Chapter 19
Chapter 21 →